Get Mystery Box with random crypto!

በየመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል ስቱዲዮቹ | Ethiopian Digital Library

በየመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል

ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው።

ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል።

እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል።

መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ።

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library