Get Mystery Box with random crypto!

ትምሕርት ቤቶች በተዘጉባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው በምስራ | Ethiopian Digital Library

ትምሕርት ቤቶች በተዘጉባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው

በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደሩ ሴት ተማሪዎችን ያለሀይባይነት ወደ ትዳር እየገፏቸው ነው፤ወላጆች ከፍተኛ ድግስ በመደገስ የኢኮኖሚ ችግር እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ነዋሪም ወላጆች ልጆቻቸውን ከት/ቤት እያስወጡ እየዳሩ ነው፤እስከ 10 ዓመት ህጻናት መዳራቸውን ማየታቸውን ገልጠዋል።

በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው፣ ሴት ተማሪዎች ወደ ጋብቻ እየገቡ እንደሆነ ነዋሪዎችና ወላጆች አመልክተዋል፤ የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ በ9ወሩ ውስጥ ከ1000 በላይ ያለእድሜ ጋብቻ ጥቆማዎች ደርሶኛል ብሏል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዶይቼ ቬሌ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት በአንዳንድ አካባቢዎች ባሉ የፀጥታ ችግር ምክንቶች ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ሥራ ባለመጀመራቸው እድሜያቸው ያልደረሰ ሴቶች ጭምር እየተዳሩ ነው፡፡ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የደጋዳሞት ወረዳ ነዋሪ በተለያዩ የክፍል ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ወደ ትዳር እየገቡ ነው፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪም አርሶ አደሩ ሴት ተማሪዎችን ያለሀይባይነት ወደ ትዳር እየገፏቸው ነው፡፡ ከፍተኛ ድግስ ስለሚያደርጉም አርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ችግርም እየደረሰበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ነዋሪም እንዲሁ ወለጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እያስወጡ እያዳሩ ነው፤ እንደአስተያየት ሰጪው፣ እስከ 10 ዓመት ህፀናት መዳራቸውን ማየታቸውን ገልጠዋል፡፡

የሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ነዋሪ ለትምህርት ያላቸው ፍላጎት ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እየቀነሰ በመሄዱ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ በትምህርት ላይ ያሉ ወጣት ተማሪዎች ወደ ትዳር እየገቡ ነው፡፡

በአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ድህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ባለፉት 9 ወራት 1 ሺህ አንድ መቶ 32 መዳር ከሚገባቸው እድሜ በታች የሆኑ ሴቶች ለመዳር መዘጋጀታቸውን ጥቆማ እንደደረሳቸው አመልክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የ335ቱ ተማሪዎች የጋብቻ ዝግጅት እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን 216 ደግሞ የእድሜ ምርመራ ተደርጎ እድሜያቸው ባለመድረሱ የትዳር ዝግጅቱ ተቋርጧል ብለዋል፡፡ያም ሆኖ 192 ሴቶች ከእድሜያቸው በታች መዳራቸውን የገለጡ ሲሆን ድርጊቱን ለመከላከል አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አንድ አንቅፋት ነው ብለዋል፡፡

በ9 ወሩ 41 ጠለፋ በክልሉ የተመዘገበ ሲሆን 354 ደግሞ አስገድዶ መድፈር ሪፖርት እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ 79 ግለሰቦች ከ3 አስከ 14 ዓመት በሚደርስ የፍርድ ቤት የእስር ቅጣት እንደተወሰነባቸውም ገልጠዋል፡፡

በአማራ ክልል መመዝገብ ከነበረባቸው 6.2 ተማሪዎች መካከል 2.6 የሚሆኑት ወደትምህርት ቤት እንዳልመጡ፣ 350 የአንደኛና 225 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ በመጋቢት 2016 ዓ ም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገልፀው እንደነበር ይታወሳል ። #DW_AMHARIC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library