Get Mystery Box with random crypto!

Big Habesha

Alamat saluran: @bighabesha_softwares
Kategori: Teknologi
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 49.70K
Deskripsi dari saluran

This is the official telegram channel of @bighabesha from Tiktok.
My YouTube channel: @bighabesha
ማንኛውም አይነት ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ቲፖች፣ ትምህርታዊ መጽሃፍትና ዶክመንተሪዎች ይለቀቁበታል።
You can talk to me here👉 @bighabesha

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 3

2024-01-19 11:33:18
እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን።
12.9K viewsBig, edited  08:33
Buka / Bagaimana
2024-01-19 07:15:29 ዛሬ አሪፍ አፕሊኬሽን እናስተዋውቃቸሁ። /አፑ Application Signal ይባላል፡፡/

Signal አፕሊኬሽን እንደ WhatsApp ፤ Facebook ፤ Skype ፤ Telegram…ወዘተ ፈጣን መልእክት(Text) መላላኪያ Application ነው፡፡

Signal አፕሊኬሽን ከሌሎቹ (WhatsApp ፤ Facebook Messenger ፤ Skype ፤ Telegram) የሚለየው ሰዎች በ Signal የሚለዋወጡዋቸው ሚስጥራዊ መልእክቶች ከሰዎቹ በስተቀር ሌላ ሶስተኛ ወገን መልእክቶችን ማየትም ይሁን ማግኘት አይችሉም፡፡ በSignal የምንለዋወጠው መልእክት ሙሉ ለሙሉ 100% ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፡፡(End-to-end encrypted)

ለምሳሌ እስካሁን ድረስ የምናውቀው በ WhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች ሙሉ ለሙሉ ሚስጥራዊ እንደሆኑ ነበረ፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ በ በ WhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች በሙሉ ፌስቡክ ኩባንያ ማወቅ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ Edward Snowden እና  Elen Musk የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ከWhatsApp ፤ Facebook Messenger ፤ Skype ፤ Telegram ይልቅ Signal አፕሊኬሽንን እንድንጠቀም ይመክራሉ፡፡

Signal አፕሊኬሽን ለ Android ፤ iPhone እና iPad እና ለኮምፒውተር እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም የሚያስፈልገው ሞባይል ስልክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡

በSignal አፕሊኬሽን አጭር መልእክቶችን ከመላላክ  ባለፈ ግሩፕ መፍጠር ያስችላል፤ቪዲዮ ኮል አለው፤የተለያዩ ስቲከሮች አሉት፤ፋይል ማስተላለፍ ይችላል..ወዘተ፡፡

የSignal አፕሊኬሽን የሚሰጣቸው ለየት ያሉ ሶስት ጥቅሞቸን ልንገራችሁ፡፦

ኛ፦ Block Screenshot

ለምሳሌ ከአንድ ሰው ጋር በ Facebook Messenger የተፃፃፋችሁትን መልእክት ያ ሰው መልእክቱን በስልኩ ስክሪን ሻት በማድረግ መረጃ ሊዝባችሁ ይችላል፡፡ Signal ላይ ግን ማንም ሰው የተፃፃፋችሁትን መልእክት ስክሪን ሻት እንዳያደርግ ብሎክ ማድረግ ይቻላል፡፡

ኛ፡- Blur Faces

በSignal ማንነታችሁን የሚገልፅ ፎቶዎች ልትላላኩ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ፎቶዋችሁን የላካችሁለት ሰው ቢያስፈራራችሁ-ለምሳሌ ሼር አረገዋለሁ ወይም ሌላ ነገር እያለ ቢያስፈራራችሁ Signal ሴቲንግ ውስጥ ገብታችሁ የላካችሁትን ፎቶ ወይም ምስላችሁ እንዳይታይ (Blur )ማድረግ ይቻላል፡፡



ኛ፡-Disappearing Messages

በSignal አፕሊኬሽን የምንለዋወጣቸው መልእክቶች የላክንለት ሰው ካነበበው በሁዋላ መልእክቶቹ ከሰውዬው ስልክ ላይ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡

Signal አፕሊኬሽንን ተጠቀሙት፡፡

አፕልኬሽኑን ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ!
https://t.me/big_habesha/163
https://t.me/big_habesha/163
13.5K viewsRed hat, 04:15
Buka / Bagaimana
2024-01-18 07:29:05
Websites for High Quality Stock Photos. /አሪፍ እና ጥራት ያላቸውን ፎቶውችን በቀላሉ በነጻ የምናገኝበት ዌብሳይቶች!

1. Pexels - A treasure trove of stunning visuals for any theme or concept.
       https://www.pexels.com/

2. Unsplash - Dive into a vast collection of artistic and diverse photos.
      https://unsplash.com/

3.  Pixabay - Where quality meets variety. Find the perfect image for any occasion.
      https://pixabay.com/

4. Magdeleine - Discover unique and captivating visuals that stand out.
     https://magdeleine.co/

5. Gratisography - Quirky and creative images that break the mold.
     https://gratisography.com/
13.2K viewsRed hat, 04:29
Buka / Bagaimana
2024-01-05 16:20:58
ለኢትዮጵያውያን ለሥራ ፍለጋ የሚረዱ የተወሰኑ ድረገጾች እና ፖርታልስ (Portals) እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1. www.ethiojobs.net

2. https://dereja.com

3. https://et.profdir.com/

4. http://Www.harmeejobs.com

5. www.ezega.com

6. www.unjobs.org

7. www.employethiopia.com

8. https://www.au.org/about/employment

9. http://www.hawassaonline.com/jobs.php

10. http://www.unicef.org/ethiopia/careers_12858.html
13.8K viewsRed hat, 13:20
Buka / Bagaimana
2024-01-05 09:23:48 የጠፋ ቴሌግራም ሚሴጅ እንዴት መመለስ ይቻላል?

ቴሌግራም ላይ በስህተት ወይም እያወቃችሁ እናንተ ወይም ቻት የሚያደርጋችሁ ሰው ያወራችሁትን ቻት delete ካደረጋችሁ መልሳችሁ ሃሳባችሁን ለመቀየር የ5 second ጊዜ ብቻ ነው ያላችሁ። Delete እያደረጋችሁ በመሃል ሃሳብ ብትቀይሩ በ5 ሰከንድ ውስጥ undo ማድረግ ትችላላችሁ። ከዛ ውጪ የጠፋ telegram message መመለስ አይቻልም።

ነገር ግን ያወራችሁትን chat የምታወሩት ሰው ምናልባት ሊያጠፋው ይችላል ብላችሁ ከጠረጠራችሁ ዳታውን ቀድማችሁ export ማድረግ ትችላላችሁ። የሚሰራው ግን ኮምፒውተር ላይ ብቻ ነው።
እንዴት እንደምታደርጉ በቅደም ተከተል ላሳያችሁ።
1. ኮምፒውተራችሁ ላይ ቴሌግራም ሶፍትዌር ጫኑና login አድርጉ።
2. Export ማድረግ የምትፈልጉትን chat ምረጡና ከላይ ያለውን 3 ነጥብ ነክታችሁ export chat history ምረጡ።
3. Chat export settings ይከፈትላችኋል export ማድረግ የምትፈልጉትን የፋይል አይነት ምረጡ። Photos, Videos, Voice messages, Video messages, stickers, GIFs, Files
የፋይል መጠኑን መጨመር መቀነስ ትችላላችሁ።
4. ከታች 4 ምርጫዎች አሉ።
Format: ዳውንሎድ የምታደርጉበት ፎርማት ምን መሆን እንዳለበት የምትመርጡበት አማራጭ ነው። HTML format, JSON format ወይም ሁለቱንም መምረጥ ትችላላችሁ።
Path: ዳውንሎድ የምታደርጉበት ፋይል የሚቀመጥበት ፎልደር path ነው።
From: ከመቼ ጀምሮ ያለውን ቻት export ማድረግ እንደምትፈልጉ የምትመርጡበት ነው።
To: እስከመቼ ድረስ ያለውን ቻት export ማድረግ እንደምትፈልጉ የምትመርጡበት ነው።
5. ከላይ ያሉትን አስተካክላችሁ ከመረጣችሁ በኋላ Export የሚለውን button ትነካላችሁ።
export አድርጎ ይጨርስላችኋል።
6. Export አድርጎ ከጨረሰ በኋላ የመረጣችሁት ፎልደር ውስጥ ገብታችሁ ሙሉ ፋይሉን ማግኘት ትችላላችሁ።
ያወራችሁት ቻት html ፋይል ስለሆነ መክፈት የምትችሉት በብሮዘር ነው።
13.9K viewsBig Habesha, 06:23
Buka / Bagaimana
2024-01-04 15:28:03
"Wi-fi" የተፈጠረው በድንገት ነው እንደሆነ ያውቃሉ የአውስታሊያ ሳይንቲስቶች ከ"Black Hole" ውስጥ የሚውጣውን Radiowave ለመሰብሰብ የሚያስችል እቃ በመስራት ላይ እያሉ ነው የተፈጠረው።
#General_Knowledge

Join Our Social Media Community
YouTube: @bighabesha
TikTok: @bighabesha
Instagram: @bighabesha
Facebook: @bighabesha1
12.8K viewsRed hat, 12:28
Buka / Bagaimana
2024-01-03 17:32:41
አውሮፕላን ላይ ስልካችንን Switch Off ወይም ፍላይት ሞድ ለምን እናደጋለን

በአውሮፕላን ስንጓዝ የተንቀሳቃሽ ስልካችን(ሞባይል) ከኔትወርክ ግንኙነት ውጪ እንዲሆን የሚያስችለውን (ፍላይት ሞድ) የጥሪ አማራጭ ካልተጠቀምን ምን ሊያስከትል እንደሚችል ያውቃሉ?

በአውሮፕላን ጉዞ ሲያደርጉ የስልክዎን የጥሪ አይነት (ፍላይት ሞድ) ላይ እንዲያደርጉ ወይም ከነጭራሹ እንዲያጠፉ በበረራ ሰራተኞች ወይም አስተናጋጆች መጠየቅ የተለመደ ነው። ይሁንና በርካቶቻችን ለምን ይሄን እንድናደርግ እንደምንጠየቅ ግን ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ለመስጠት ስንቸገር እንስተዋላለን።

አንዳንዶቻችንም “ስልኮቻችን በበረራ ወቅት ከኔትወርክ ግንኙነት ውጪ ካላደረግናቸው በአውሮፕላኑ የኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ላይ ከፍተኛ ችግርን በመፍጠር የመከስከስ አደጋን ሊያስከትሉ ይችላሉ” የሚል የተሳሳተ ግምት እንወስዳለን።

ይሁንና እውነታው እንደተባለው የሞትና የህይወት ጉዳይ ሳይሆን ከዚህ የተለየ ነው። የሞባይል ስልካችን እንደተባለው “ፍላይት ሞድ” ላይ ካልተደረገ ከስልኩ የሚወጡ የድምፅ ሞገዶች በአብራሪው ላይ ረብሻን ሊፈጥሩ ይችላሉ።

ከዚህ ባለፈም የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ስርዓቱን በድምፅ የማወክ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም ነው የተነገረው። ምናልባትም ተንቀሳቃሽ ስልካችን ከድምፅ መሳሪያዎች አቅራቢያ በሚሆንበት ጊዜ ያልተለመደና የሚረብሽ ድምፅን አስተውለን ሊሆን ይችላል። ይህ የሚከሰተው ከስልኩ የሚወጣው የድምፅ ሞገድ (electromagnetic radiation) ጠንካራ በመሆኑ ሳቢያ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተመረቱ የሚገኙ በቴክኖሎጂ የተራቀቁ ስማርት ስልኮች ለዚህ ሲባል አንስተኛ የድምፅ ሞገድን ብቻ ሊያስከትሉ በሚችሉበት ደረጃ በመመረት ለገበያ በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።

#Tech_Tips
13.7K viewsRed hat, 14:32
Buka / Bagaimana
2024-01-01 10:08:28 10 በጣም ጠቃሚ ድረገፆች

1. themarkup.org/series/blacklight = Real Time website privacy inspector. ማንኛውንም ድረገፅ ከመክፈታችሁ በፊት ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቅማችኋል።
2. codingame.com = ጌም እየተጫወታችሁ ኮዲንግ የምትለማመዱበት
3. Remotists.com = በአለም አቀፍ ደረጃ remote ስራዎችን search የምታደርጉበት
4. hacksplaining.com = Hacking ቀላል በሆነ መንገድ የምትማሩበት
5 Typelit.io = የተለያዩ ፅሁፎችን Type እያደረጋችሁ የምትለማመዱበት
6. coveryourtracks.eff.org = የምትጥቀሙት browser ምን አይነት መረጃ አሳልፎ እንደሚሰጥና track ያደርግ እንደሆነ check የምታደርጉበት
7. www.startrek.com/ የቴክ ዜናዎች ዶክመንተሪዎችና ታሪኮች በፅሁፍ የምታገኙበት
8. musclewiki.com = የሰውነት እንቅስቃሴ በምናደርግበት ጊዜ ምን አይነት ስፖርት መስራት እንዳለብንና የትኛውን የሰውነታችን ክፍል ለማዳበር እንደሚጠቅመን ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያሳየን
9. codepen.io = የተለያዩ ኮዲንግ ፕሮጀችቶችን የምታገኙበት እንዲሁም ድረገፁ ላይ ኮድ ፅፋችሁ run ታደርጉበታላችሁ።
10. litsolutions.org = የተለያዩ መፅህፍትን ጥያቄዎች መልስ የምታገኙበት

Join Our Social Media Community
YouTube: @bighabesha
TikTok: @bighabesha
Instagram: @bighabesha
Facebook: @bighabesha1
14.7K viewsBig Habesha, 07:08
Buka / Bagaimana
2023-12-31 18:25:33 ማንኛውንም ሙዚቃ ወይም መዝሙር በነፃ Online ወይም offline የምታዳምጡበት App

https://t.me/big_habesha/160
13.0K viewsBig, 15:25
Buka / Bagaimana
2023-12-31 15:58:50
ማንኛውንም ጥያቄ (ግራመር ማስተካከል)፣ምግብ አሰራር፣ School question ባጠቃላይ በምስሉ ላይ ያሉትን Features የያዘ ሁሉንም ሚሰራ CHAT GPT.
13.4K viewsRed hat, 12:58
Buka / Bagaimana