Get Mystery Box with random crypto!

የጠፋ ቴሌግራም ሚሴጅ እንዴት መመለስ ይቻላል? ቴሌግራም ላይ በስህተት ወይም እያወቃችሁ እናንተ | Big Habesha

የጠፋ ቴሌግራም ሚሴጅ እንዴት መመለስ ይቻላል?

ቴሌግራም ላይ በስህተት ወይም እያወቃችሁ እናንተ ወይም ቻት የሚያደርጋችሁ ሰው ያወራችሁትን ቻት delete ካደረጋችሁ መልሳችሁ ሃሳባችሁን ለመቀየር የ5 second ጊዜ ብቻ ነው ያላችሁ። Delete እያደረጋችሁ በመሃል ሃሳብ ብትቀይሩ በ5 ሰከንድ ውስጥ undo ማድረግ ትችላላችሁ። ከዛ ውጪ የጠፋ telegram message መመለስ አይቻልም።

ነገር ግን ያወራችሁትን chat የምታወሩት ሰው ምናልባት ሊያጠፋው ይችላል ብላችሁ ከጠረጠራችሁ ዳታውን ቀድማችሁ export ማድረግ ትችላላችሁ። የሚሰራው ግን ኮምፒውተር ላይ ብቻ ነው።
እንዴት እንደምታደርጉ በቅደም ተከተል ላሳያችሁ።
1. ኮምፒውተራችሁ ላይ ቴሌግራም ሶፍትዌር ጫኑና login አድርጉ።
2. Export ማድረግ የምትፈልጉትን chat ምረጡና ከላይ ያለውን 3 ነጥብ ነክታችሁ export chat history ምረጡ።
3. Chat export settings ይከፈትላችኋል export ማድረግ የምትፈልጉትን የፋይል አይነት ምረጡ። Photos, Videos, Voice messages, Video messages, stickers, GIFs, Files
የፋይል መጠኑን መጨመር መቀነስ ትችላላችሁ።
4. ከታች 4 ምርጫዎች አሉ።
Format: ዳውንሎድ የምታደርጉበት ፎርማት ምን መሆን እንዳለበት የምትመርጡበት አማራጭ ነው። HTML format, JSON format ወይም ሁለቱንም መምረጥ ትችላላችሁ።
Path: ዳውንሎድ የምታደርጉበት ፋይል የሚቀመጥበት ፎልደር path ነው።
From: ከመቼ ጀምሮ ያለውን ቻት export ማድረግ እንደምትፈልጉ የምትመርጡበት ነው።
To: እስከመቼ ድረስ ያለውን ቻት export ማድረግ እንደምትፈልጉ የምትመርጡበት ነው።
5. ከላይ ያሉትን አስተካክላችሁ ከመረጣችሁ በኋላ Export የሚለውን button ትነካላችሁ።
export አድርጎ ይጨርስላችኋል።
6. Export አድርጎ ከጨረሰ በኋላ የመረጣችሁት ፎልደር ውስጥ ገብታችሁ ሙሉ ፋይሉን ማግኘት ትችላላችሁ።
ያወራችሁት ቻት html ፋይል ስለሆነ መክፈት የምትችሉት በብሮዘር ነው።