2023-12-12 06:59:23
Hacking ውድ የ Big Habesha ቤተሰቦች በዚህ Episode በጣም የተለመዱት የሳይበር ጥቃት አይነቶቾን እናያለን።
Distributed denial of service (Ddos) በዚህ የጥቃት አይነት ሀከሩ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ ማንኛውንም ሲስተም ለጊዜው ወይም ላልተወሰነ ጊዜ በማስተጓጎል ሲስተሙ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት እንዳይችል የሚደረግበት የሳይበር ጥቃት ነው። ይህ የጥቃት አይነት ሲስተሙን ባላስፈላጊ ትእዛዞች (Commands) በማጨናነቅ ከተጠቃሚዎች የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎችን መመለስ እንዳይችል ያረገዋል።
Man in the Middle በዚህ የጥቃት አይነት ሀከሩ በቀጥታ እርስ በእርሳቸው እንደሚያወሩ በሚያምኑ ሁለት ወገኖች መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች መሀል በመግባት መልክቶቹን ማንበብ ወይም ከፈለገ የሚቀይርበት ጥቃት ነው። ይህ ሀከር ከአንዱ የሚመጣውን መልእክት እንዳሻው ቀይሮ ለሌላኛው ይልካል።
Phishing and Spear Phishing Phishing በኢንተርኔት ግንኙነት ውስጥ እንደ ታማኝ አካል በመመሰል እንደ Username ፣ Password እና የCredit Card መረጃዎችን ለማግኘት የሚደረግ የማጭበርበር ሙከራ ነው። በተለምዶ ይህ ጥቃት በኢሜል እና በSMS መልእክት ይፈፀማል።
Drive by Attack በዚህ የጥቃት አይነት ሀከሩ ደህንነታቸው ያልተጠበቀ ድረገፆችን ይፈልጉና በአንዱ ላይ በHTTP ወይም Php ኮድ ማልዌር ይተክላሉ። ይህ ማልዌር ጣቢያውን በሚጎበኝ ሰው ኮምፒተር ላይ በቀጥታ ራሱን ይጭናል ወይም ተጠቂውን ሀከሩ ወደሚፈልገው ድረገፅ ይወስደዋል።
Password attacks ይህ የጥቃት አይነት የአንድን ሰው Password ለማግኘት የሚደረግ ጥረት ሲሆን ተጠቂው ቦታ በመሆን ለመገመት መሞከርንም ይጨምራል። ሁለት ታዋቂ Password Hacking አይነቶች አሉ።
የመጀመሪያው brute force ሲሆን በዚህ የጥቃት አይነት በጣም ብዙ የቃላት እና የቁጥሮች ስብስብ ተራ በተራ በማስገባት አንዱ ይሰራል በሚል የሚሞከር የጥቃት አይነት ነው።
ሌላኛው ደግሞ ከተጠቂው ስም ፣ የሥራ ዘርፍ ፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ወይም ተመሳሳይ ነገሮች ጋር የሚዛመዱ የይለፍ ቃሎችን የያዘ ዲክሽነሪ በመጠቀም ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል።
SQL Injection Attack በዚህ የጥቃት አይነት ሀከሩ የውሂብ-ተኮር መተግበሪያዎችን ለማጥቃት የሚያገለግል የኮድ የሚጭንበት ቴክኒክ ነው። ይህ ኮድ በውስጡም አደገኛ SQL Statements ለማስፈፀም ይውላል (ለምሳሌ የመረጃ ቋቱን ይዘቶች ለሀከሩ ለመላክ)። የSQL Injection ጥቃት በብዛት ዳታቤዞችን ለማጥቃት ያገለግላል።
Eavesdropping Attack በዚህ የጥቃት አይነት ሀከሩ በክፍት ኔትዎርክ የሚደረጉ ግንኙነቶችን በመጥለፍ የሰዎችን ሚስጥር የመስማት በተጨማሪም በሚደረጉት ግንኙነቶች ውስጥ የሚተላለፉ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚሰርቅበት ነው።
14.4K viewsRed hat, 03:59