Get Mystery Box with random crypto!

ማይክሮሶፍት አዲሱን VASA-1 አስተዋወቀ ማይክሮሶፍት ሪሰርች ቡድን VASA-1 ብሎ የሰየመው | Big Habesha

ማይክሮሶፍት አዲሱን VASA-1 አስተዋወቀ

ማይክሮሶፍት ሪሰርች ቡድን VASA-1 ብሎ የሰየመውን የአንድን ሰው ፎቶ እና የንግግር ድምጽ በመጠቀም ወደ ከፍተኛ ደረጃ እውነተኛ ቪዲዮ የሚቀይር ቴክኖሎጂን ይፋ አድርጓል።

ቴክኖሎጂው አንድ ነጠላ ፎቶ እና የንግግር ድምጽ በመጠቀም በትክክለኛ የከንፈር ድምጽ በማመሳሰል፣ ህይወት ያለው የፊት ባህሪ እና በእውነተኛ ጊዜ የሚፈጠሩ ተፈጥሯዊ የጭንቅላት እንቅስቃሴዎች ያለው ፍፁም እውነት የሚመስል የንግግር የሚታይበት ቪዲዮ አዘጋጅቷል።

ከላይ የተያያዘው ቪድዬ አንድን ፎቶ በመጠቀም የተሰራ ቪድዬ ሲሆን ብዙዎች እውነተኛነቱ አሳማኝ ሆኖ አግኝተውታል።
#Tech_News #Microsoft