Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌግራም መስራች Pavel Durov አስገራሚው የህይወት ታሪክ ክፍል 2 ዲሮቭና ወንድሙ የተወሰ | Big Habesha

የቴሌግራም መስራች Pavel Durov አስገራሚው የህይወት ታሪክ
ክፍል 2

ዲሮቭና ወንድሙ የተወሰኑ የVK ታማኝ ሰራተኞችን ወደ ኒዮርክ በማስኮብለል በሚስጥር ሲሰሩት የነበረውን ይህን ሚዲያ (telegram) በይፋ ስራውን አስጀመሩ።

ቴሌግራምም  ዋና መስርያ ቤቱን ጀርመን በርሊን በማድረግ ስራውን በይፋ ጀመረ።
ቴሌግራም ለተወሰኑ አመታት ምንም አይነት ገቢ ስለማያስገባ ዲሮቭ ለስራ ማስኬጃ በየወሩ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከራሱ ኪስ ያወጣ እንደነበር በተለያዩ ድረገፆች ተገልጿል።

ከሌሎች የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች በተሻለ የተጠቃሚዎቹን መረጃ ሚስጥራዊነት  እንደሚጠብቅ የሚነገርለት ይህ አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ በመወደድ ስኬት ማስመዝገብ ጀመረ። ከመንግስታዊ ተፅዕኖም ነፃ በመሆኑና ከዋና ተገዳዳሪው ዋትሳፕ የተሻለ ብዙ ፊቸሮች ስለጨመረ በብዙዎች ዘንድ ለመወደድ በቃ።

እስካሁን ድረስም የተለያዩ የሚስጥራዊነት ፊቸሮችን እየጨመረ በአስገራሚ ፍጥነት እያደገ ይገኛል።

እጅግ የተራቀቀ የሚስጥራዊነት ስላለውም የአለማችን መሪዎች፣ አደገኛ ፅንፈኛ ቡድኖች እንዲሁም የአንባገነን ሃገራት ተቃዋሚዎች ይህን አፕሊኬሽን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመለዋወጥና መሳሪያ ለመሻሻጥ ይጠቀሙበታል። 

በሚቀጥሉት ጥቂት አመታትም በተጠቃሚ ቁጥር በሜታ ስር ከሚተዳደሩት facebook messenger እና WhatsApp ሊበልጥ እንደሚችል ይጠበቃል።
በአሁኑ ሰአት ዋና መስሪያ ቤቱን በዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ዱባይ ከተማ በማድረግ ከተራ የመልዕክት መለዋወጫ አፕሊኬሽንነት ከፍ በማለት የክሪፕቶከረንሲ ቢዝነስ አካቶ እየሰራ ይገኛል። 

የዲሮቭ የግል ስብዕናና የሃብት መጠን
እንደፎርብስ መረጃ ዱሮቭ በ2024 የ15.5 ቢሊየን ዶላር ባለጸጋ ሲሆን ያላገባና የሁለት ልጆች አባት ነው። በአሁኑ ሰአት ኑሮውን ዱባይ ላይ አድርጓል። በ2021 የUAE ዜግነት የተሰጠው ሲሆን ከUAE በተጨማሪ የፈረንሳይም ዜግነትም አለው።
Libertarian (የግል ነፃነትን የሚያቀነቅን)፣ teetotaler (መጠጥ በፍፁም የማይጠጡና የማይደግፉ) እንዲሁም Vegetarian እንደሆነ ይነገርለታል። ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሃገራት መዞር የሚወድ ሲሆን The Matrix ፊልም ላይ እንዳለው ኒዮ ሁሌም ጥቁር ልብስ መልበስ ያዘወትራል።

በግል ያገኛቸው ሽልማትና እውቅናዎች
2014  "The most promising Northern European leader under 30".
2017 "The world economic forum the young Global Leaders".
2018, The Union of Kazakhstan's Journalists, "for his principled position against censorship and the state's interference into citizens' free online correspondence."
2018, Fortune magazine "The most influential young people in business."
2023, Arabian business, "The most powerful entrepreneur".


እኛስ ከእሱ ምን እንማራለን?
ሃሳባችሁን ኮመንት ላይ አስቀምጡልን።