Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ አሪፍ አፕሊኬሽን እናስተዋውቃቸሁ። /አፑ Application Signal ይባላል፡፡/ Sign | Big Habesha

ዛሬ አሪፍ አፕሊኬሽን እናስተዋውቃቸሁ። /አፑ Application Signal ይባላል፡፡/

Signal አፕሊኬሽን እንደ WhatsApp ፤ Facebook ፤ Skype ፤ Telegram…ወዘተ ፈጣን መልእክት(Text) መላላኪያ Application ነው፡፡

Signal አፕሊኬሽን ከሌሎቹ (WhatsApp ፤ Facebook Messenger ፤ Skype ፤ Telegram) የሚለየው ሰዎች በ Signal የሚለዋወጡዋቸው ሚስጥራዊ መልእክቶች ከሰዎቹ በስተቀር ሌላ ሶስተኛ ወገን መልእክቶችን ማየትም ይሁን ማግኘት አይችሉም፡፡ በSignal የምንለዋወጠው መልእክት ሙሉ ለሙሉ 100% ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፡፡(End-to-end encrypted)

ለምሳሌ እስካሁን ድረስ የምናውቀው በ WhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች ሙሉ ለሙሉ ሚስጥራዊ እንደሆኑ ነበረ፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ በ በ WhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች በሙሉ ፌስቡክ ኩባንያ ማወቅ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ Edward Snowden እና  Elen Musk የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ከWhatsApp ፤ Facebook Messenger ፤ Skype ፤ Telegram ይልቅ Signal አፕሊኬሽንን እንድንጠቀም ይመክራሉ፡፡

Signal አፕሊኬሽን ለ Android ፤ iPhone እና iPad እና ለኮምፒውተር እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም የሚያስፈልገው ሞባይል ስልክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡

በSignal አፕሊኬሽን አጭር መልእክቶችን ከመላላክ  ባለፈ ግሩፕ መፍጠር ያስችላል፤ቪዲዮ ኮል አለው፤የተለያዩ ስቲከሮች አሉት፤ፋይል ማስተላለፍ ይችላል..ወዘተ፡፡

የSignal አፕሊኬሽን የሚሰጣቸው ለየት ያሉ ሶስት ጥቅሞቸን ልንገራችሁ፡፦

ኛ፦ Block Screenshot

ለምሳሌ ከአንድ ሰው ጋር በ Facebook Messenger የተፃፃፋችሁትን መልእክት ያ ሰው መልእክቱን በስልኩ ስክሪን ሻት በማድረግ መረጃ ሊዝባችሁ ይችላል፡፡ Signal ላይ ግን ማንም ሰው የተፃፃፋችሁትን መልእክት ስክሪን ሻት እንዳያደርግ ብሎክ ማድረግ ይቻላል፡፡

ኛ፡- Blur Faces

በSignal ማንነታችሁን የሚገልፅ ፎቶዎች ልትላላኩ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ፎቶዋችሁን የላካችሁለት ሰው ቢያስፈራራችሁ-ለምሳሌ ሼር አረገዋለሁ ወይም ሌላ ነገር እያለ ቢያስፈራራችሁ Signal ሴቲንግ ውስጥ ገብታችሁ የላካችሁትን ፎቶ ወይም ምስላችሁ እንዳይታይ (Blur )ማድረግ ይቻላል፡፡



ኛ፡-Disappearing Messages

በSignal አፕሊኬሽን የምንለዋወጣቸው መልእክቶች የላክንለት ሰው ካነበበው በሁዋላ መልእክቶቹ ከሰውዬው ስልክ ላይ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡

Signal አፕሊኬሽንን ተጠቀሙት፡፡

አፕልኬሽኑን ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ!
https://t.me/big_habesha/163
https://t.me/big_habesha/163