Get Mystery Box with random crypto!

ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

Logo saluran telegram mahibereestifanos111 — ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
Logo saluran telegram mahibereestifanos111 — ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏
Alamat saluran: @mahibereestifanos111
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 1.39K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻይናል መንፈሳዊ ትምህርቶች,ግጥሞች,ያሬዳዊ ዜማዎች,ምስባክ,መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋዎች(በአውዲዮና በቪዲዮ), እና የመሳሰሉት ይለቀቁበታል
Chaayinaalii kana keessatti barnoota amanta,walaloo,faaruu yaareed,misbaakii ,faaruu qooqa garaa garaatin (audio fi video),fi kan kana fakkaatan itti gadhiifamu

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2023-05-09 07:52:23 #እናቱ_እናቴ_ልደትሽ_ልደቴ !

ለእናትነት ክብር - እርሱ ከመረጠሽ
በዮሐንስ በኩል - ለእኔ ከተሰጠሽ
እኔም እርሱን ጌታ - ብዬ ከተቀበልሁ
ማዳኑን አምኜ - በሕጉ ስር ከዋልሁ
እናቱን እናቴ - ብየ ለመቀበል...
ጥያቄ ልደርድር? ለምን? እንዴት? ልበል?

ልጅሽ በምድር ላይ - ሥጋሽን በመልበስ
አዳምን ሊያድነው - ለእኛም ጽድቅን ሊያወርስ
የረገጠው መሬት - የቆመበት ቦታ
ከቤተልሄም ዋሻ - እስከ ጎለጎታ
ቅዱስ ከተባለ - ውሎ ያደረበት
ልዩ ክብር ካለው - የተሰቀለበት...
አንችማ እናቱ - ማህፀን ዓለሙ
የሰውነት ልኩ - ሥጋውና ደሙ
እንዴት አትከብሪ!? እንዴት አትቀደሽ!?
እንዴት አትወደጅ!? እንዴት አትወደሽ!?

እንኳንስ ለእኔና...
ለእርሱም ለጌታችን - ፈጣሪ ለሆነ
እናቱ መባልሽ - ይህ እውነት ከሆነ
እናቴ መሆንሽ - እንዴት አልታመነ???

በሥጋ ያይደለ - በረቀቀ መንፈስ
እናቴ ሆነሽኝ - ያንችን ክብር ብወርስ
ይሄንን መታደል - እንዴት እገፋለሁ?
እናቱ እናቴ ነሽ! - ተቀብየሻለሁ!!!

ፈጣሪን ልትወልጅው - አምላክን ልታ’ዥው
ሰማይና ምድር የማይወስኑትን - በእቅፍሽ ልትይዥው
ከድንግልና ጡት - ወተት ልታጠቢው
የዓለሙን መጋቢ...
ከደኃ ማጀትሽ - ሲራብ ልትመግቢው
እናት አባትሽን - ከእስር ልታስፈቺ
የክፋትን አባት - በፍቅር ልትረቺ
ከሀና ከኢያቄም - የተወለድሽ አንቺ
እናትና ድንግል - ንግሥትና አገልጋይ
ሰማየ ሰማያት - ጽርሐ አርያም ሆይ!
የአንቺ ግሩም ልደት - ለእኔም ነው ልደቴ
የጥምቀት መሥራቹ - ልጅሽ ነው አባቴ
ዳግም የተወለድሁ - ከውኃና መንፈስ
ባንቺ መወለድ ነው - የአዳም ተስፋው ሲደርስ
ሕይወት የሆነልን - የልጅሽ ሥጋና ደም
ከአንቺው ነው የነሳው - ከላይ አልወረደም
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እና ነሽ - ልደትሽ ልደቴ

ቅድስተ ቅዱሳን - ንጽሒተ ንጹሐን
ማሕጸኑ ለጽድቅ - እናቱ ለብርሃን
ሰማየ ሰማያት - ታናሽ ብላቴና
ከእያቄም ወሀና - ተወለደሻልና
ዓለም ብርሃን አየ - ውስጥሽ ባለው ፀሐይ
አዳም ቀና አለ - ተስፋ ብርሃኑን ሊያይ
ፍጥረታት በሙሉ - ከሰማይ ከምድር
በደስታ ተመሉ - ልደትሽ ሲነገር
ተወለደሻልና - የፀሐይ እናቱ
ጽርሃሐ-አርያም ሆንሽ - ብላቴናይቱ !

(አበው ስለክብርሽ - ቃላት አጠራቸው
ስለ ደም ግባትሽ - ምሳሌ ጠፋቸው
እኔ ግን ደፋሩ - እዘባርቃለሁ
ባልበሰለ ብዕር - ቃላት እመርጣለሁ
በተንሸዋረረ ዓይን - ክብርሽን አያለሁ
ምልጃሽን እያሰብሁ - በተስፋ እኖራለሁ።)

የብርሃን እናቱ - የፀሐይ ምሥራቁ
የአዳም ሙሉ ተስፋ - የሰይጣን መብረቁ
ስለ አንቺ መወለድ - ዓለም ተፈጠረ
ስለ አንቺ መወለድ - የሰው ልጅ ከበረ
አዳምና ዘሩ - በኃጢአት ቢረክሱ
በአንቺ መወለድ - ግን በክብር ነገሡ
በአንቺ ልዩ ልደት - አዳም አምላክ ሆነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ክብራችን ገነነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ዲያብሎስ ታሰረ
በአንቺ ልዩ ልደት - ባሪያ መሆን ቀረ
እኔም ደፋር ሆንኩኝ - ፍርሃት ተሰወረ
ባዶው አዕምሮዬ - ክብርሽን ነገረ፡፡

ሰማይና ምድር - ልደትሽን ሲያከብሩ
ሊቃውንት ሲቀኙ - መላእክት ሲዘምሩ
ክብርሽን ተማምነው - በምልጃሽ ያደሩ
በምህረት ቃል ኪዳን - ለክብር ሲጠሩ
እንደልጅነቴ ለእኔም - እንዲደርሰኝ
እንባሽን አስታውሶ - ልጅሽ እንዲምረኝ
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
የአንቺ መወለድ ነው - የጽድቅ መሠረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እናቴ ነሽ - ልደትሽ ልደቴ ነው፡፡


ምንጭ :- የተዋህዶ ልጆች ግሩፕ

እንኳን አደረሳችሁ

ደቂቀ እስጢፋኖስ


ሼር ሼር ሼር

ደስ የሚሉ የተዋሕዶ ትምህርቶችንና ግጥሞችን ለማግኘት ይሄንን ሊንክ ይንኩና join ይበሉ


https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
63 viewsedited  04:52
Buka / Bagaimana
2023-05-08 09:16:02
173 views06:16
Buka / Bagaimana
2023-05-08 05:42:18 ሚያዝያ 30


እንኳን ለወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ የእረፍት በአል በሰላም አደረሳችሁ

183 viewsedited  02:42
Buka / Bagaimana
2023-05-06 12:08:19
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ በአይሁድ እርቦ (jewish quarter ) ያዩት ድንቅ ስእል ታሪኩ ከላይ ተጽፏል
255 views09:08
Buka / Bagaimana
2023-05-06 06:02:46 ከዓመት እስከ ዓመት ግርግር በማያጣትና ሁሌም በሰውና በገበያተኛ በተጨናነቀችው ኢየሩሳሌም ውስጥ እየተጓዝን ነው:: ጥንታዊትዋ የኢየሩሳሌም ከተማ በአሁኑ ሰዓት በአራት ሩቦች ተካፍላ ትተዳደራለች:: የክርስቲያን እርቦ ፣ የሙስሊሞች እርቦ ፣ የአርመኖች እርቦ እና የአይሁድ እርቦ ይባላሉ::

ለሦስቱ አብርሃማውያን እምነቶች (Abrahamic religions) ለአይሁዳዊነት ለክርስትናና ለእስልምና ትልቅ ፋይዳ ባላት ኢየሩሳሌም "አርብ አርብ" ብቻ ሳይሆን ሁሌም ሽብርና ግርግር አለ::  በሁሉም ሩቦች ተሳላሚዎች ፣ ጎብኚዎች ፣ ሻጮች ፣ ገዢዎሽ እስከ እኩለ ሌሊት ይርመሰመሳሉ:: 

ዘንድሮ እግር ጥሎኝ ከአንድ ወዳጄ ጋር በአይሁድ እርቦ (Jewish quarter) በኩል ሳልፍ አንድ ልብ የሚነካ ሥዕል ዓይኔ ውስጥ ገባ:: ሥዕሉን ሳይ ዕንባ በዓይኔ ሞላ:: የኢሳይያስ 53ቱን የሕማም ሰው ፣ የማይናገረውን በግ በአንገቱ የእሾህ አክሊል ጌጥ አድርገውለት እንዲህ ሆኖ ሳየው ችዬ የማላነበውን ኢሳይያስ 53 በሥዕል ሲያመጣብኝ ከማልቀስ ውጪ ምንም አቅም አልነበረኝም::

ነቢዩ ኢሳይያስ ሳይናገር በፊት የሚቀበለው እንደሌለ አውቆ "የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል?" ብሎ የተጨነቀበትን ይህን አስጨናቂ ራእይ እንዴት እንረሳዋለን? ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባስ በቀር ኢሳይያስ 53 ን አንብቦ "ማን አምኖአል?" (ሐዋ. 8:26) የእግዚአብሔር ክንዱ የተባለ ክርስቶስስ ለማን ተገልጦአል?

በግርፋቱ ብዛት ፊቱ በደም ተለውሶ "ባየነው ጊዜ እንወደው ዘንድ ደም ግባት የለውም" የተባለበትን ውበቱ ስለ እኛ የጠፋው የሕማም ሰው እንዴት ከሕሊናችን ተሰወረ?

"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።ተጨነቀ ተሠቃየም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም" የሚለው ቃል ምንኛ ያስጨንቃል? ቆስሎ የሚፈውስ ታምሞ የሚያድን ታስሮ ነፃ የሚያወጣውን የእግዚአብሔር በግ ለመግለፅ ቃላት አቅም ቢያጥራቸው እንዲህ በብሩሽ ኃይል ተሥለው ሳያቸው ሁሉን ነገር ዘነጋሁት::

አንድ ልብሱ በቀለም ያደፈ ሰው በሥዕል ጋለሪው ደጃፍ ቁጭ ብሎ ይፈርማል:: እንደ መታደል ሆኖ ሰውዬው የሥዕሉ ባለቤት UDI MERIOZ ነበረ:: ቀርቤ ስለ ሥዕሉ የተሰማኝን ስነግረው እሱም ስሜቱ ተነካ:: "ይሄንን ሥዕል እኔ ብሥለውም የእኔ ፈጠራ አይደለም:: ሸራውን ወጥሬ በቀለም ላይ የሠራሁት እኔ ነኝ:: ነገር ግን ከመሣሌ በፊት በተደጋጋሚ በሕልሜ አየው ነበር:: የሣልሁትም ያየሁትን ነው" አለኝ:: ሥዕሉንም ፈርሞ ለእኔና ለወዳጄ ሠጠን::

ቅዱስ ኤፍሬም "ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል?" እንዳለው የጌታን መከራ የሚገልፅ አንደበት የሚሥለው ብሩሽ ባይኖርም ለአፍታ ግን እንዲህ በየሰዉ ላይ ባሳረፈው ጸጋ ሕማሙን ያስታውሰናል::

ይህ የበገና መዝሙር ግጥም ግን ከሕሊናዬ መጣ

"ያ ሁሉ መከራ እንዴት ይግባ ልቤ
  አልበጠስ አለኝ የኃጢአት መረቤ

ተው ልቤን ስበረው ልመንህ አጥብቄ
  መቼ ሕይወት ሆነኝ ቃልህን ማወቄ
  ቃሉን ተናጋሪ ምግባር የሌለኝ
ተገርፎአል ተሰቅሎአል የምል ብቻ ሆንኩኝ" (ዘማሪት አዳነች አስፋው)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Share share

https://t.me/mahibereestifanos111

https://t.me/mahibereestifanos111
280 views03:02
Buka / Bagaimana
2023-05-05 12:38:32
በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ስለ ወደደን አዳነን



እንኳን ለቸሩ መድኃኔዓለም ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የቀራንዮ ላይ ውለታህ እንደምን ይረሳል
ቀንና ሌሊት ሁሌ ይታወሳል
ለሰው ያለህ ፍቅር እጅጉን ይለያል

የመድኃኔዓለም ምህረቱ አይለየን አሜን
288 views09:38
Buka / Bagaimana
2023-05-04 20:11:20 አባታችን ሆይ


በዘወትር ፀሎታችን ከለመድነው ፀሎታ አባታችን ሆይ የሚለው ፀሎታችን ከፈጣሪ የተሰጠን ልዩ ፀሎት ነው

ሉቃስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።
² አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
³ የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤
.......................

ዘወትር ይሄን ፀሎት ከመልመዳችን የተነሳ ቃላቶቹን እንኳን ባለማስተዋል የምንልበት ጊዜ ይበዛል
ግን ሁሉንም እንተውና ስለ መጀመሪያው ቃል ብቻ እንነጋገር አባታችን ሆይ
አባት ማለት መከታ ማለት ነው፣ አባት ማለት ተስፋ፣ አባት ማለት መሰረትዠ፣ አባት እሩሩህ ማለት ነው
አባት ማለት.........

“አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤”
— መዝሙር 104፥13

እግዚአብሔር ከአባት የበለጠ አባት እንደሆነ የማያደራድር ሐቅ ነው ትልቁ ጥያቄ ግን እኛ ልጆቹ ነን

እግዚአብሔር በአርዓያው ወዶና ፈቅዶ የፈጠረን ከፍጥረታት ሁሉ አክብሮ በቅዱሳን እጆቹ የፈጠረን በቀራንዮ ላይ ደሙን ያፈሰሰልን ለኛ ካለው የአባትነት ፍቅር የተነሳ ልጆቹ እንድንሆን ስለሚፈልግ ነው
እኛ ግን ልጅ መሆን ተስኖናል ልጅ ለአባቱ ይታዘዛል ልጅ የአባቱን ቃል ያከብራል ልጅ የአባቱን ስም ያስጠራል እኛ ግን ለአባታችን መታዘዝ ካቆምን ዘመናት አልፈዋል እኛስ የአባታችንን ቃላት ማክበር ካቆምን ከራርሟል
ታዲያ እንደምን አባታችን ሆን ብለን በሙሉ አንደበታችን እንጠራዋለን በእርግጥ ምንም እንኳን እኛ አባትነቱን ብንክድም እሱ ግን ዛሬም በአባትነት አይን በፍቅር አይኖቹ ያየናል ነገር ግን እኛ የሱን አባትነት እንደምንፈልገው ሁሉ እሱም ልጅነታችንን ይፈልጋል አይ አልታዘዝም ስንልም አባት ልጁን እንደሚቀጣ እሱም ይቀጣናል እንድንጠፋ ሳይሆን ወደሱ እንድንመለስ

“እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።”
— ምሳሌ 3፥12

ወዳጄ አባታችን ሆይ በለህ ስትፀልይ አንተም ልጅ ሆነህ መገኘትህን አትርሳ አባትህን አክብረው አባትህን ውደደው ለሱ ተገዛ እሱም ደሞ የማያልቀውን በረከት ይሰጥሃል የምትጠይቀውን ሁሉ ያለማንገራገር ይሰጥሃል


ደቂቀ እስጢፋኖስ።

ሼር ያድርጉ ይቀላቀሉን

ቻይናላችን
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111


ግሩፕ
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
2.8K views17:11
Buka / Bagaimana
2023-05-03 22:53:41 የተወደዳችሁ የደቂቀ እስጢፋኖስ ቻናል ቤተሰቦች discuss ግሩፑ ተከፍቷል እየገባችሁ ሰዎችን add+ አድርጉ


https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos
272 viewsedited  19:53
Buka / Bagaimana
2023-05-03 22:52:20 ቤትህን አጽዳ

አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው  ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል? ይፈልጋል
278 views19:52
Buka / Bagaimana
2023-05-03 16:22:38 Gooftaa koo maal siif kennu?

Yeroo tokko namni tokko suuraa Iyyasuus Kiristoos fuuldura dhaabatee Gooftaa! Maal narraa barbaadda? Maal akkan siif godhu barbaadda?...Natti himi, dungoo dheeraa akka koo dheeratu akkan siif fidu ni barbaaddaa? qaba. Gooftaan immoo, "dammi ibsaa tolchu kan kooti, buddeenni damma kan kooti" jedhee deebiseef. Namichis, "Tolee egaa, tajajila dilbataaf kan ta'u foonii fi dhigasaa kan ta'un fidee dhufa" jedhee deebiseef. Gooftaan keenyas "Qamadii foon qopheessuuf itti fayyadaman illee kan kooti" jedhee deebiseef. Namichis sana booda "Ergasii hiyyeessa gargaaruuf Birrii 1000,000 siif kenna" jedhee deebiseef Iyyasuus Kiristoos. Wantoonni ati qaba jettu hundinuu kan kooti; Lafti fi hunduu kan Waaqayyooti, biyyi lafaa fi warra ishee keessa jiraatan hundaati. Far. 24:1). Namichis, "Gooftaa, maal akkan siif fidu barbaadda?" Iyuesuus Kiristoos immoo "Ilma koo laphee kee naaf kenni, siif dheebodheera, jaalala keetiif gara fannoottin deeme" jedheen. Waaqayyo waan qabnu hunda dura nu barbaada. Osoo isaaf of hin kennine yoo dadhabne iyyuu wanti barbaachisu xiqqoo ykn waan tokko qofa" (Luq. 10:42). Beekumsa keenya kennine, qarshii keenya kennine, humna keenya yoo kennine fi nuti kan isaa yoo hin taane maal fayyada? Cubbuun isa irraa waan adda nu baasu iccitii hafuuraatiin isa waliin tokko ta’uun nuuf wayya, akka gaabbiidhaan laphee keenya isaaf dabarsinuuf. Gaabbiidhaan of haa dhiheessinee waaqa nu uumetti laphee keenya haa kenninu.

Waaqayyoon galanni haa ta'u


Share godhaa
Nu waliin ta'aa
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111
276 viewsedited  13:22
Buka / Bagaimana