Get Mystery Box with random crypto!

አባታችን ሆይ በዘወትር ፀሎታችን ከለመድነው ፀሎታ አባታችን ሆይ የሚለው ፀሎታችን ከፈጣሪ የተሰ | ደቂቀ እስጢፋኖስ ijoollee isxifaanoos🙏⛪️🙏

አባታችን ሆይ


በዘወትር ፀሎታችን ከለመድነው ፀሎታ አባታችን ሆይ የሚለው ፀሎታችን ከፈጣሪ የተሰጠን ልዩ ፀሎት ነው

ሉቃስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።
² አላቸውም፦ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
³ የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤
.......................

ዘወትር ይሄን ፀሎት ከመልመዳችን የተነሳ ቃላቶቹን እንኳን ባለማስተዋል የምንልበት ጊዜ ይበዛል
ግን ሁሉንም እንተውና ስለ መጀመሪያው ቃል ብቻ እንነጋገር አባታችን ሆይ
አባት ማለት መከታ ማለት ነው፣ አባት ማለት ተስፋ፣ አባት ማለት መሰረትዠ፣ አባት እሩሩህ ማለት ነው
አባት ማለት.........

“አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤”
— መዝሙር 104፥13

እግዚአብሔር ከአባት የበለጠ አባት እንደሆነ የማያደራድር ሐቅ ነው ትልቁ ጥያቄ ግን እኛ ልጆቹ ነን

እግዚአብሔር በአርዓያው ወዶና ፈቅዶ የፈጠረን ከፍጥረታት ሁሉ አክብሮ በቅዱሳን እጆቹ የፈጠረን በቀራንዮ ላይ ደሙን ያፈሰሰልን ለኛ ካለው የአባትነት ፍቅር የተነሳ ልጆቹ እንድንሆን ስለሚፈልግ ነው
እኛ ግን ልጅ መሆን ተስኖናል ልጅ ለአባቱ ይታዘዛል ልጅ የአባቱን ቃል ያከብራል ልጅ የአባቱን ስም ያስጠራል እኛ ግን ለአባታችን መታዘዝ ካቆምን ዘመናት አልፈዋል እኛስ የአባታችንን ቃላት ማክበር ካቆምን ከራርሟል
ታዲያ እንደምን አባታችን ሆን ብለን በሙሉ አንደበታችን እንጠራዋለን በእርግጥ ምንም እንኳን እኛ አባትነቱን ብንክድም እሱ ግን ዛሬም በአባትነት አይን በፍቅር አይኖቹ ያየናል ነገር ግን እኛ የሱን አባትነት እንደምንፈልገው ሁሉ እሱም ልጅነታችንን ይፈልጋል አይ አልታዘዝም ስንልም አባት ልጁን እንደሚቀጣ እሱም ይቀጣናል እንድንጠፋ ሳይሆን ወደሱ እንድንመለስ

“እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።”
— ምሳሌ 3፥12

ወዳጄ አባታችን ሆይ በለህ ስትፀልይ አንተም ልጅ ሆነህ መገኘትህን አትርሳ አባትህን አክብረው አባትህን ውደደው ለሱ ተገዛ እሱም ደሞ የማያልቀውን በረከት ይሰጥሃል የምትጠይቀውን ሁሉ ያለማንገራገር ይሰጥሃል


ደቂቀ እስጢፋኖስ።

ሼር ያድርጉ ይቀላቀሉን

ቻይናላችን
https://t.me/mahibereestifanos111
https://t.me/mahibereestifanos111


ግሩፕ
https://t.me/dekikeestefanos
https://t.me/dekikeestefanos