Get Mystery Box with random crypto!

ምርጧ ሚስት ምን አለች? 'እዚህ ቤት ማን አለ' 'ባሌ ስራ | ፍቅርን በትዳር ውስጥ

ምርጧ ሚስት

ምን አለች?


"እዚህ ቤት ማን አለ"


"ባሌ ስራ ሄዶ  ሲመለስ ከቤቱ፣
እኔን ያጣኝ ጊዜ ምን ይላል አንጀቱ?

አወ ክፍት ይላል  እኔንማ  ሲያጣ፣
ቤቱ ባዶ ሆኖ  ሲያገኝ ጣራ ብቻ፣
እኔው ስጠፋበት  የአይኑን ማረፊያ፣

ስለዚህ

ክብሬና ማረጌ   የኔ ደስታዬ፣
ባሌን ማስደሰት ነው በመሆን ከቤቴ፣

ባሌ ቢከፋብኝ  እኔ ምን ልደሰት፣
ይርቀኛል  እንጂ የአላህ እራህመት።

ዙረት ምን ሊሰራ ወድህ ምን ሊጠቅመኝ፣
ከቤቴ እወጣለሁ  ምንስ ሊያስደስተኝ፣

ደስታዬ ያለው  ከባሌ ጋር እንጂ፣
የአላህ እዝነት ያለው  ከቤቴ ውስጥ እንጂ፣
ለኔ ሰገነቴ  የባሌ ቤት  እንጂ፣
የዞርኩበትማ  ይቀራል  ከደጂ።

ስለዚህ  ውዴዋ እጠብቃሀለሁ፣
ቤቴን አሳምሬ  እቀበልሀለሁ።
ክብርና ማረጌ መሆንክ አውቃለሁ፣
ካንተጋራ ኑሪ  መሞትን እሻለሁ፣
እንዳትከፋብኝ  ሁሉን እጥራለሁ፣
ከጎንህ ነኝ ሁሌ ውዴ እወድሀለሁ፣
አላህ በአዘዘኝ ቀጥብዬ እቆማለሁ፣
በአሄራም ካንተጋር መሆንን እሻለሁ፣

በስህተት ካጠፋሁ አደራ አውፍ በለኝ፣
እዚህ ቤት ማን አለ ያለሁህ እኔነኝ፣
ውዴ እወድሀለሁ አንተም እዘንልኝ።"


ይህንን  ትላለች ምርጧ ሚስት ሁልጊዜ

እህቶቻች  አላህ ሷሊህ  ያድርጋችሁ

Channel
https://t.me/LoveOfMarriage