Get Mystery Box with random crypto!

'አቡ ጁሐይፋህ ወሀብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ 'ነቢዩ ( | ፍቅርን በትዳር ውስጥ

"አቡ ጁሐይፋህ ወሀብ ኢብኑ ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦

"ነቢዩ (ﷺ) ሰልማንን እና አቡ ደርዳዕን (ረዲየላሁ ዐንሁ) በወንድማማችነት አቆራኙ። ሰልማን አቡ ደርዳዕን ለመጉብኘት ሲሄድ ኡሙ ደርዳዕ ራሷን ጥላ ተመለከታት፥ "ምን አገኘሽ?" ሲል ጠየቃት። "ወንድምህ አቡ ደርዳዕ ለዚች ዓለም ቅንጣት ያህል ግድ የለውም" አለችው። አቡ ደርዳዕ መጣ። ምግብ አዘፋጀለትና "ብላ እኔ ፆመኛ ነኝ" አለው። "አንተ ካልተመገብክ አልመገብም" አለ ሰልማን። ተመገበ-አቡ ደርዳዕ ። አመሻሽ ላይ አቡ ደርዳዕ የሌሊት ሶላት ለመስገድ ተዘጋጀ። "ተኛ" አለው። ተኛ። እንደገና ለሶላት ተነሳ።"ተኛ" አለው። በሌሊቱ መጨረሻ ላይ "አሁን ተነስ" አለው። ሁለቱም ሰገዱ። ሰልማን እንዲህ አለ "ጌታህ በአንተ ላይ መብት አለው፥ ነፍስህ በአንተ ላይ መብት አላት፥ ቤተሰቦችህም በአንተ ላይ መብት አላቸው፥ ለእያንዳንዱ ባለመብት መብቱን አድርስ።" ነብዩ(ﷺ) ዘንድ መጣና ይህንኑ አወሳላቸው፡፡ "ሰልማን እውነቱን ነው" አሉ መልዕክተኛው (ﷺ)፡፡"
(ቡኻሪ ዘግበውታል)
==========================




Jone