Get Mystery Box with random crypto!

======== ተራርቀን ነበር====== አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ። ===== | ፍቅርን በትዳር ውስጥ

======== ተራርቀን ነበር======





አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ።

======== ተራርቀን ነበር========

ፍቅርን በትዳር ውስጥ ማጣጣም ተስነኖነን፣
ጋብቻን በመጥላት ሀገርን አቋርጠን፣
ከአድማሱ ወዳ ጨለማውን መርጠን፣
ከትዳር አለም ጋር ተራርቀን ነበር።

ያለውቀት ያላግባብ መሰረቱን ጥለን፣
የእስልምናን ህግ አሽቀንጥረን ጥለን፣
ስንጓዝ ስንጓዝ ጥፍጥናው ጠፍቶብን፣
ጉዞውን መራራ ኮሶ አልብሶብን፣
ተራርቀን ነበር እረቀን ጋብቻን ።


ግን
በእውቀት ታንፀን በሸሪዓ ታጥረን፣
አውነታው ሲገለፅ ውሸት አመድ ሲሆን፣
መልካም ትዳር ነበር የኢማን መሰረት፣

አወ
ፍቅርን ለማጣጣም እንደማር ወለላ፣
በትዳር ውስጥ ነው የሌለው አምሳያ፣

በትዳር ውስጥ ፍቅርን የምታጣጥሙ፣
የለገሳችሁን አላህን ተገዙ፣
አልሀሙዱሊላህ በማለት ደጋግሙ።

ያላገባችሁም አላህን ለምኑ፣
ከጣፈጠው ህይወት በሀላል ተጋቡ።
ትረዱታላችህ ህይወትን ስትኖሩ።
ተራርቀን ነበር በኋላ እንዳትሉ።




___

አቡ ተቅይ ቃዒድ
======================
ሼር እና ጆይን
https://t.me/LoveOfMarriage


https://t.me/PomeChannelGroup