Get Mystery Box with random crypto!

ነብዩሏህ_አደም (ዐለይሂ ሰላም )          ክፍል   አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አደምን ዐ | 📚🍃ቀሶሱል አንቢያ 📝👇

ነብዩሏህ_አደም (ዐለይሂ ሰላም )

         ክፍል

  አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አደምን ዐ ሰ ለመፍጠር በፈለገ ግዜ ጂብሪልን ወደ መሬት ወርዶ አፈር ዘግኖ እንዲያመጣ ላከው።ጅብሪልም ወደ መሬት ከወረደ በኋላ ከመሬት አፈር ሊዘግን ሲል መሬትም፦"እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው።

ጅብሪልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ ተመለሰ።
አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ እጠበቃለሁ ስትለኝ ተመለስኩ" አለው።

ከዚያም አላህ ሚካኢልን ላከው።ሚካኢልም ትእዛዙን ሊፈፅም ወደ ምድር ሲወርድ መሬትም፦" እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው።

ሚካኢልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ ተመለሰ።
አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ እጠበቃለሁ ስትለኝ ተመለስኩ" አለው።

በመጨረሻም አላህ አዝራኢልን ላከው አዝራኢልም ተልዕኮውን ሊፈፅም ምድር ላይ ወረደ'ና አፈር ሊዘግን ሲል ምድር፦" እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው።

አዝራኢልም፦"እኔ እራሴ የአላህን ትዕዛዝ ሳልፈፅም ከመመለስ በአላህ እጠበቃለሁ" ብሏት አፈር ከተለያየ ቦታ መዘጋገን ጀመረ።

ከጥቁሩም፣ከነጩም፣ከቀዩም...ዘገነ።ለዛ ነው የሰው ልጆች መልክም የተለያየው።ከዚያም አፈሩን ይዞ አላህ ዘንድ ሲቀርብ አላህም፦" መሬት ምን እያለችህ ነው አፈሩን ይዘህ የመጣሄው?በአለህ እጠበቃለሁ እንደትቀነሰኝ ስትል!እኔም በአለህ እጠበቃለሁ የአሏህን ትዛዝ ከመፈፀም በዬ ይዠ መጣሁ፡፡እንደዛ እያለችህ አፈሩን አንተ እንዳመጣህ ሁላ ነፍሳቸውንም እንድታወጣ አንተን ወክዬሀሁ" አለው።

ከዚያም ከምድር የመጣው አፈር ረጥቦ ጭቃ ሲሆን ግዜ አላህ ለመላዕክቶቹ፦"እኔ ከጭቃ ሰውን ልፈጥር ነው። ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ።" ብሎ መልዕክት አስተላለፈላቸው።

ከዚያም አላህም ኢብሊስ እንዳይኩራራ አደምን በእጁ ፈጠረው።ከዚያም ለ40 አመት ያህል ጭቃው ቅርፅ ብቻ ሆኖ ከረመ።እና መላዕክት በዛ በኩል ሲያልፉ አደምን ሲያዩት በጣም ይፈሩ ነበረ...ነፍስም አልገባለትም ነበር።

ከሁሉም በላይ እሚፈራው ኢብሊስ ነበር።ኢብሊስ ሁሌ ከአደም ጭቃ አጠገብ ሲያልፍ መታ አድርጎት ነበር ሚያልፈው።ያን ግዜ ሸክላ ሲመታ እሚወጣው ድምፅ ይሰማ ነበር

ከዚያም ኢብሊስ ከአደም ጭቃ ጎን ላይ ቆሞ፦"አንተማ ለሆነ ነገር ነው የተፈጠርከው" እያለ በአፉ እየገባ በመቀመጫው ይወጣ ጀመር...ለመላዕክትም፦"እኔ በዚህ ላይ ከተሾምኩ አጠፋዋለሁ" በማለት ይዝት ጀመር።

አላህም በአደም ገላ ላይ ነፍስ መንፋት በፈለገ ግዜ መላዕክትን፦"ልክ ሩሁን/ነፍሱን እንደነፋሁለት ሰጋጆች ሆናችሁ አጎብድዱ" ብሎ አዘዛቸው።

መላዕክትም ዝግጁ ሁነው መጠባበቅ ሲጀምሩ አላህ በአደም ሩሁን/ነፍሱን መንፋት ሲጀምር ገና ነፍሱ በአደም ጭንቅላት በኩል ስትገባ አደም አስነጠሰው።
መላዕክትም፦"አልሀምዱሊላህ በል" አሉት።
አደምም፦"አልሀምዱሊላህ" ሲል...
አላህ ደግሞ፦"ጌታህ ይማርህ" ብሎ መለሰለት።

ከዚያም ነፍሱ አይኑ ጋ ስትደርስ የጀነት ውስጥ ፍራፍሬዎችን ተመለከተ አንገቱ ላይ ስትደርስ ደግሞ ፍራፍሬዎችን መብላት አሰኘው'ና ገና ነፍሱ እግሩ ላይ ሳትደርስ ሄዶ ለመብላት ተጣደፈ።

ነፍሱ መላ ሰውነቱ ላይ ስትሰራጭ ከመላዕክት ሁሉ ቀድሞ ሱጁድ ያደረገለት ኢስራፊል ነበር። ከዚያም አላህ ለአደም፦"ሂድ እነዛን ሰላም በላቸው'ና ምን ብለው እንደሚመልሱልህ አድምጥ" ብሎ ላከው።

ሄዶ ሰላም ሲላቸውም መላዕክትም፦"ወዐለይኩሙሰላም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ" ብለው መለሱለት።
አላህም ለአደም፦"አደም ሆይ! ካሁን በኋላ ይህ ያንተ እና የዝርዮችህ ሰላምታ ሆኖ ይዘልቃል" አለው።

አደምም፦"ጌታዬ ዝርዮቼ እነ ማን ናቸው?" ብሎ ጠየቀው።
አላህም፦"ከሁለቱ እጆቼ ምርጥ" አለው።
አደምም፦"ቀኝህን መርጫለሁ ሁለቱም እጆችህ ቀኝ ናቸው" ብሎ ሲል...

አላህም እጁን ሲከፍትለት አደም እስከቂያማ ድረስ ያሉ ልጆቹን ሁሉ ተመለከተ።በዚያም መሀል አንድ ብርሀናማ ሰው ተመለከተ'ና፦"ያ አላህ ይህ ማን ነው?" ሲል ጠየቀ።
አላህም፦"እሱ ልጅህ ዳዉድ ነው"ብሎ መለሰለት።
አደምም፦"ጌታዬ ለዚህ ልጄ እድሜውን ስንት ነው ያደረግክለት?" ብሎ ሲጠይቅ...
አላህም፦"60 ነው" አለው።
አደምም፦"ጌታዬ ከኔ እድሜ 40 ቀንስ'ና ለሱ ጨምረህ መቶ ሙላለት" አለው።(ለአደም የተመደበለት እድሜ 1000 ነበር)
አላህም እሺ ብሎ ሞላለት'ና ምስካሪ መላዕክቶችንም አደረገ።

በአላህ ፍቃድ ክፍል ነገ

    ቀ
          ጥ
                ላ
                     ል..............

አንበበው ዝም አይበሉ
#ሼር አርጉ


#ተ_ቀ_ላ_ቀ_ሉ

ቻናላችን join

https://t.me/YereSulwedajoch_12
https://t.me/YereSulwedajoch_12