Get Mystery Box with random crypto!

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተወካዮች ጋር | OMN-OROMIA MEDIA NETWORK OFFICIAL

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተወካዮች ጋር ሊወያዩ ነው።
===============================================

ማይክ ሐመር በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተወካዮች ጋር ሊወያዩ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቋል።

ለሚቀጥሉት ዘጠኝ ቀናት በሎስ አንጀለስ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ከትግራይና ከሶማሊ ማኅበረሰብ የተውጣጡ ተወካዮችን አግኝተው እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ረቡዕ ግንቦት 02/ 2015 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነትን ጨምሮ በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

በተጨማሪም አምባሳደሩ ከቀጠናው የተውጣጡ የሴቶች መሪዎች ጥምረት ‘ዩናይትድ ዊሜን ኦፍ ዘ ሆርን’ በተባለው የሲቪክ ድርጅት አዘጋጅነት በአሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋርም ውይይት ያደርጋሉ።

ቦብ ሆፕ ፓትሪዮቲክ አዳራሽ ላይ በሚካሄደው ውይይትም “ሰላምን በማስፈን እና የሴቶችን አቅም በማጎልበት” ላይ እንደሚያተኩር ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የወጣም መረጃ ያሳያል።