2024-05-18 14:50:20
#ወሳኝ_መልዕክት ከፍተኛ አመራሮች ትግሉን ገምግሙት !! .. 1) አገዛዙ በየቀኑ ስብሰባና ግምገማ ላይ ነው። ግምገማ የኢህአዴግ ፈጠራ አይደለም። ከፖለቲካ ጋር የኖረ ነው። ትግሉን መገምገም ግድ የሚያስብሉ ጉዳዮች ሞልተዋል።
2) የህዝብ ግንኙነት ስራ ብለው ለዩቱዩብ በሚጠቅማቸው መልኩ የሚያቀርቡት አካላት በዝተዋል። ለአብነት ያህል የቀበሌ ካድሬ መገደሉን በትልቅ ዜናነት የሚሰሩ፣ ተቀነደሸ፣ ወዘተ የሚሉ አካላት የፍትህና ህልውናን ጉዳይ የመገዳደልና የበቀል አስመስለው እያቀረቡት እያበላሹት ነው። የአማራው ትግል ከግዙፉ አላማው ይልቅ በካድሬና ሚሊሻ መገደል እንዲሳል እየተደረገ ነው።
3) ጉዞ ወደ አራት ኪሎ እየተባለ ተመልሶ ደግሞ የወረዳን ከተማ አራትና አምስት ጊዜ እየያዙ አለኝ የሚሉትን አመራር ማስመታት፣ አገዛዙ ሲመለስ የሚቀጣው ህዝብ እንዲማረር እያደረገ ነው። ከተማ ተቆጣጥሮ ሲወጣ ሕዝብ የአገዛዙን ዱላ የሚሰጋ ከሆነ በሂደት "አያድነኝም፣ አይቆምልኝም" ከማለት አልፎ "እንግዲህ መጡ፣ ሊያስጨርሱን ነው" ወደማለት ይሄዳል።
4) ገና ጦርነቱ መሃል ላይ አንዱን ፋኖ አመራር ከሌላኛው፣ አንዱን የሚዲያ ሰው ከሌላው የሚያጋጩ ጉዳዮች የበዙት አንድም የአገዛዙ እጅ፣ በዋነኛነት ግን የተጠኑ አካሄዶች አለመኖራቸው ነው።
5) በቅርቡ አገዛዙ ባደረገው ግምገማ 41 በመቶ የአማራ ክልል መዋቅር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለፋኖ መረጃ እየሰጠብኝ ነው ብሏል። ከዛ በፊት ሙሉ መዋቅሩን ከስልጣን አንስቷል። ይህ በሆነበት ከካድሬ እስከ ሚሊሻ በአንድነት ልግጠመው ማለት ስልት ማጣት ነው።
6) አልፎ አልፎ ከትህነግ ጋር ለመስራት የሚደረጉ አካሄዶች እንዳሉም ይታያሉ። ደብረፅዮንና ጌታቸው ረዳ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ከአብይ ጋር፣ ታደሰ ወረደ ጦር ኃይሎችና ደብረዘይት ከብርሃኑ ጁላ ጋር እየዋሉ ከትህነግ ጋር አብሬ እሰራለሁ የሚል አካል ምን አስልቶ እንደሆነ ግራ ያጋባል። የትህነግ ዩቱዩበሮች ሲሰድቡት የከረሙት ፋኖ ደጋፊ መስለው ሲቀርቡ አራት ኪሎና ጦር ኃይሎች ከብልፅግና ጋር ከሚውሉት የትህነግ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች የተለዩ ህወሓቶች የሚመስለው ካለ ራሱን ይመርምር።
7) ትህነግ የአማራ ክልሉን ጦርነት የሚፈልገው አማራውን ለማዳከም ነው። የትህነግ የሁሌም አላማ የአማራ ግዛቶችን መንጠቅ ነው። ይህን ካሳካ በኋላ ተሳልቆ ብቻ አይሄድም። የዘር ፍጅት ፈፅሞብኛል እያለ በሀሰት ሲከሰው የኖረው ፋኖን ነው። ትህነግ በኃይል ለመያዝ የሚፈልጋቸው ግዛቶች አካባቢ ፋኖ ጦርነት እንዲከፍትለት ይፈልጋል። ይህ የስህተት መንገድ ነው። ከህዝብ ጋር ማጋጨት ብቻ ሳይሆን ኢህአፓ በሶማሊያ ጦርነት ስሙ እንደጠፋው መጥፎ አጋጣሚም ነው። የአማራ ግዛቶች ቀይ መስመሮቻችን ናቸው የሚል ቀይ መስመሩን ማስታወስ አለበት።
8) አገዛዙ ህዝብን በድህነት ማጥ ውስጥ ከትቶ ማሸነፍ ይፈልጋል። ትግል ውስጥ ላለው ደግሞ ህዝብ ስንቁም መሸሸጊያውም ይሆናል። ስለሆነም አገዛዙ የማይፈልገውን በጦርነት ወቅትም ቢሆን ህዝብ አርሶ፣ ነግዶ እንዲበላ ማድረግ ያስፈልጋል። ካልሆነ ሰብአዊ ቀውሱን አንችለውም። በትግራይ ከጦርነት በኋላ የእርስ በእርስ መገዳደል፣ ስርቆትና ስደት ቅጥ አጥቷል። በጦርነት መሃልም ይህን ማሰብ ያስፈልጋል። እንዲያውም ትህነግ ቦታ ፈልጎ እንጅ በአንድም የትግራይ ከተማ ሳይዋጋ ነው ይህ ሁሉ ቀውስ የደረሰው።
9/ በጦርነቱ መሃል እርስ በእርሱ የሚራኮተው መአት ነው። ያልተወገዘ የፋኖ አመራር፣ እስረኛ፣ ምሁር፣ ተቋም፣ የሚዲያ ሰው ወዘተ የለም። ይህ ውጥንቅጥ ያልተገመገመ ትግል ውጤት ነው። ሲገመገም "እከሌ ይህን አጥፍቷል" ይባላል። እንዳይደግመው ይደረጋል። አሁን ያጠፋው ጥፋቱን እያስተባበለ፣ የተቹት ላይ ሌላ መለስተኛ ጦርነት እየከፈተ ነው የቀጠለው። አደገኛ ነው። ቆም ብሎ መገምገም፣ ጥርት ማድረግ ያስፈልጋል። ዋጋ እየተከፈለበት፣ ህዝብ እየተሰቃየ ግምገማ እየፈራ የሚቀጥል አካል የአማራን የህልውና ትግል ወደ እርስ በእርስ ንትርክ ከማውረድ የዘለለ የሚፈይደው ነገር አይኖርም።
ትግል በየጊዜው ይገመገማል። ያልተገመገመ ትግል እዳ ያመጣል። በተለይ እንደ ሕዝብ!
@Getachew Shiferaw
ሉሲ ድንቅነሽ ኢትዮጵያ
ወጥር ጀግናዬ ትግሉ እስከ ቀራኒዮ ነው
እየጋለ የሚሄድ እንጂ ሚቀዝቀዝ ትግል አልተጀመረም YOUTUBE
13.1K viewsedited 11:50