Get Mystery Box with random crypto!

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አካል ጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር የተጠየቀ ቢሆንም የ | Ethiopian Digital Library

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አካል ጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር የተጠየቀ ቢሆንም የተሰጠዉ ምላሽ የሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አካል ጉዳተኞችን ሙሉ በሙሉ ያካተት አለመሆኑን በመገንዘብ ለጠየቅነው ጥያቄ የተሰጠን ምላሽ  የአካል ጉዳተኛን ሰብዓዊ መብት የሚጥስ መሆኑ እጅግ አሳዛኝ ነዉ ሲሉ የገለፁት የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አባይነህ ጉጆ ናቸው፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን ምላሽ በመገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቀረበው ጥያቄ መሰረት የሚፈለገውን ያህል ርቀት ለመሄድ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግሯል ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም አካል ጉዳተኞችን በስርዓተ ትምህርቱ በኩል አካታች ለማድረግ እንዲያስችል ለአመራሮች በቂ ግንዛቤ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል ሀላፊው፡፡

አሐዱም የአካል ጉዳተኞችን ሰብዓዊ መብት ከማስጠበቅ አንጻር ምን እየሰራችሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብት ስራ ክፍል ዳይሬክተር ሜቲያ ቱምሳን ጠይቋል፡፡

ኃላፊዋ በምላሻቸውም ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ ነው ለማለት ያስቸግራል ነው ያሉት፡፡ #አሐዱ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library