Get Mystery Box with random crypto!

ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገ | Ethiopian Digital Library

ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።

በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት እና ጥበቃ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ታደሰ፣ የምዝገባ ሥርዓቱን ለመጀመር 10 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ ይህ በጀት በተለያዩ አካላት መዋጮ እንደሚሸፈንም ጠቁመዋል።
ይህ ‘ብሔራዊ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል ምዝገባ ሥርዓት’ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተደረገ ጥናት ከጠቅላላ የአገሪቱ ሴቶች 35 በመቶዎቹ የተለያዩ ዓይነት ፆታዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱባቸው ያሳያል።

‘ብሔራዊ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል ምዝገባ ሥርዓት’ የተሰኘው ሥርዓቱ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች በሕግ ከታሰሩ እና ቅጣት ከተላለፈባቸው በኋላም ለዘለዓለም ተጠያቂ የሚያደርግ እና “ከተመረጡ” ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶች የሚያገል መሆኑ ታውቋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library