Get Mystery Box with random crypto!

በ2017 ትምህርት ዘመን በ11ኛ ክፍል የሥራና ተግባር ትምህርት የሚጀመርባቸውን የሙያ ዘርፍ እና | Ethiopian Digital Library

በ2017 ትምህርት ዘመን በ11ኛ ክፍል የሥራና ተግባር ትምህርት የሚጀመርባቸውን የሙያ ዘርፍ እና አይነቶች ዝርዝር

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር በቁጥር 12/242/322/16 በቀን መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በ2017 ትምህርት ዘመን በ8 የሙያ ዘርፍ ውስጥ 12 የሙያ ዓይነቶችን ለማስጀመር ዝርዝር ተልኮልናል፡፡

ስለሆነም በ2017 ትምህርት ዘመን ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥራና ተግባር ትምህርት ሙያ ትምህርት ስለሚጀምሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ባላቸው አቅም፣ በአካባቢያቸውን ጸጋ ልየታ በማድረግ የሙያ ዘርፍ እና ዓይነት በመምረጥ ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰብን የሙያ መስኮችና ዓይነቶቹን ከዚህ ሸኚ ደብዳቤ ጋር 2 ገጽ አባሪ በማድረግ የላክን መሆኑን አሳስባለሁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library