Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል መሬት ያልወሰዱ መምህራን ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ታዘዘ በኦሮሚያ | Ethiopian Digital Library

በኦሮሚያ ክልል መሬት ያልወሰዱ መምህራን ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ታዘዘ

በኦሮሚያ ክልል የመኖሪያ ቤት የሚሰሩበት መሬት ላልወሰዱ የክልሉ መምህራን ቦታ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ትእዛዝ መስጠታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አድርጎ 8 የውሳኔ ሀሳቦችን ያስተላለፈ ሲሆን ከ8ቱ ነጥቦች አንዱ በከተማ ቤት መስሪያ ቦታ ላልወሰዱ መምህራን በአስቸኳይ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም መምህራኑ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መመሪያ ወጥቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ከቆይታ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እገዳ ተጥሎ እንደነበርና በክልሉ ት/ት ቢሮ ጥያቄ መሰረት ዳግም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለመምህራኑ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ መሰጠቱ ተጠቁሟል። ጉዳዩም ተፈፃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ትዕዛዝ መስጠቱም ተገልጿል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library