Get Mystery Box with random crypto!

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተ | Ethiopian Digital Library

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ Freshman ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸሁን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከመጋቢት 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ አባይ ግቢ

በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለአንደኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። #BahirDarUniversity

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library