Get Mystery Box with random crypto!

የ2016 ፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል (ለአዲስ | Ethiopian Digital Library

የ2016 ፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

6ኛ ክፍል (ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
አማርኛ, እንግሊዘኛ, ሒሳብ, አካ/ሳይንስ እና ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም)

8ኛ ክፍል (ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
አማርኛ, እንግሊዘኛ, ሒሳብ, ሶሻል ሳይንስ, አጠ/ሳይንስ, የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም)

12ኛ ክፍል
በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው:: እነሱም :-

ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
እንግሊዝኛ, ሒሳብ, ባዮሎጅ, ፊዚክስ, ኬሚስትሪ, ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
እንግሊዝኛ, ሒሳብ, ታሪክ, ኢኮኖሚክስ, ጅኦግራፊ, ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

የፈተና ዝግጅት:-
የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ
ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ -11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::
ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል::

ሁሉም ፈተናዎች በሰኔ ወር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library