Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎች ላይ የተመዘገቡ ዝቅተኛ ውጤቶች የትምህርት ማህበረሰቡን አንቅቷል | Ethiopian Digital Library

በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎች ላይ የተመዘገቡ ዝቅተኛ ውጤቶች የትምህርት ማህበረሰቡን አንቅቷል

በ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎች ላይ የተመዘገቡ ዝቅተኛ ውጤቶች የትምህርት ስርዓቱ "የወደቀባቸውን" መሰረታዊ ችግሮች በግልጽ ከማሳየት ባለፈ የትምህርት ማህበረሰቡን ማንቃታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

የመግቢያ ፈተናዎቹ ውጤት ማሽቆልቆል ትምህርት ቤቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የተማሪዎች ወላጆች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ማንቃቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ በትምህርት ስርዓቱ ላይ የተወሰዱ ማሻሻያዎች አውንታዊ ለውጦችን እያመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የለውጦቹን ፍሬ በምልዕት ለማየት ግን ጊዜ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ የተመዘገቡት ዝቅተኛ ውጤቶች ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ከመላክ ባለፈ ትምህርታቸውን በቅርበት እንዲከታተሉ በር መክፈቱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አንስተዋል፡፡

ይህ ገንቢ ልምድ ወላጆች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከትምህርት ቤቶች እና ከመምህራን ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ማስቻሉን "በትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ በግልጽ መታየቱን አመላክተዋል፡፡

የመለኪያ ፈተናዎቹ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በስርዓት እንዲከታተሉ፣ መምህራን በኃላፊነት ስሜት እንዲያስተምሩ፣ ርዕሳነ መምህራን የትምሀርት ሂደቱን በአግባቡ እንዲመሩ መልካም ጅምሮችን መፍጠራቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library