Get Mystery Box with random crypto!

የሩሲያዉ ቢትክላስተር በኢትዮጵያ የቢትኮይን የመረጃ ማዕከል ማቋቋሙን አሳወቀ! በኢትዮጵያ የቢትኮ | Addis መረጃ™

የሩሲያዉ ቢትክላስተር በኢትዮጵያ የቢትኮይን የመረጃ ማዕከል ማቋቋሙን አሳወቀ!

በኢትዮጵያ የቢትኮይን ማይኒንግ የመረጃ ማዕከል ማቋቋሙን ያሳወቀዉ ቢትክላስተር በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቮልቴጅ ማከፋፈያ ጣቢያ ባለበት ቂሊንጦ አከባቢ መሆኑን ገልጿል።

የሩሲያው የቢትኮይን ማይኒንግ አቅራቢ ድርጅቱ አዲሱ የመረጃ ማዕከል ሥራዉ ከወር በኃላ እንደሚካሄድ በመግለፅ አሁን ላይ በ 30,000 ካሬ ሜትር ላይ ትራንስፎርመሮች የማገናኘት ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟ።

በቢትኮይን የሚፈፀሙ ግብይቶች አስተማማኝ እና እምነት የሚጣልባቸው መሆናቸዉን ለማረጋገጥ የማረዳ ስርዓት መሆኑ የተነገረለት የመረጃ ማዕከሉ 100 ፐርሰንት የኤሌክትሪክ ኃይል ከታዳሽ የኃይል ምንጮች በተለይ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚቀርብ መሆኑን አሳዉቋል። በኢትዮጵያ 120 ሜጋ ዋት የቢትኮይን የመረጃ ማዕከል ለማቋቋም የወሰነዉ ቢትክሉስተር ለሀገሪቱ ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም አለዉ ሲልም ገልጿል።

Via Capital
@Addis_Mereja