Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ከቦንድ ባለቤቶች እየተደራደረች ነው! ኢትዮጵያ ለቦንድ ባለቤቶች 33 ሚሊዮን ዶላር የወ | Addis መረጃ™

ኢትዮጵያ ከቦንድ ባለቤቶች እየተደራደረች ነው!

ኢትዮጵያ ለቦንድ ባለቤቶች 33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ ክፍያ ሳትፈጽም ቀርታ ዕዳ መክፈል ከተሳናቸው ሀገራት ጎራ ብትመደብም ሀገሪቱ ለገባችበት ቅርቃር መፍትሔ ለማበጀት ድርድር እየተደረገ ነው። ታኅሳስ 1 ቀን 2016 መከፈል የነበረበት ወለድ በዩሮ ቦንድ ውል መሠረት የነበረው የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜ አብቅቷል።

ክፍያው ሳይፈጸም ወይም የገንዘብ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት እና የቦንድ ባለቤቶች ከአንዳች ሥምምነት ሳይደርሱ የእፎይታ ጊዜው በማብቃቱ ኢትዮጵያ ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ ዕዳቸውን መክፈል ከተሳናቸው ሀገራት ጎራ ተመድባለች። ኢትዮጵያ ወለድ በቀነ-ገደቡ ሳትከፍል ከቀረች በኋላ በመንግሥት እና በቦንድ ባለቤቶች መካከል የአከፋፈል ሽግሽግ ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝ ዩኒቨርሳል ኢንቨስትመንት በተባለ ኩባንያ በኩል የኢትዮጵያ ቦንድ ባለቤት የሆነው ካፒቱሉም አሴት ማኔጅመንት ለዶይቼ ቬለ አረጋግጧል።

መቀመጫውን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ያደረገው ካፒቱሉም አሴት ማኔጅመንት ኩባንያ የፈንድ ማኔጀር የሆኑት ቲዎዶር ኪርሽነር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የቦንድ ባለቤቶች የየራሳቸውን ምክረ-ሐሳብ እንዳቀረቡ ለዶይቼ ቬለ በኢ-ሜይል በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል። “አሁን ባለው ዋጋ ያን ያህል የተራራቁ አይደሉም” ያሉት ኪርሽነር የአከፋፈል ሽግሽግ ላይ የሚደረገው ድርድር ዛምቢያ ካለፈችበት ተመሳሳይ ሒደት በጣም ፈጥኖ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተስፋቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ:-

https://p.dw.com/p/4ad8G?maca=amh-RED-Telegram-dwcom

@Addis_Mereja