Get Mystery Box with random crypto!

#ያየሁሽ_ቀን_ድባብ በተንቦለቦለው የከርቤ መአዛ ይታወቀኝ ጀመር አንቺ ስትመጪ አካሌ ሲወዛ የሻ | 🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻

#ያየሁሽ_ቀን_ድባብ

በተንቦለቦለው የከርቤ መአዛ
ይታወቀኝ ጀመር አንቺ ስትመጪ አካሌ ሲወዛ

የሻከረው ፊቴ የደረቀው ቆዳ
የለበስኩት ኩታ የልብሴ ቀዳዳ

አንቺ ስትመጪ በአስማት ተሰፋ
ባንቺ መምጣት ብቻ እንባ ሀዘኔ ጠፋ

ያየሁሽ ቀን ድባብ ያገኘሁሽ ለታ
ከኔ ተለይቶ ወዳንቺ ሲያከንፈው የልቤን ትርታ

ተመለስ ብለውም ከዳኝ እንደ ባንዳ ጥሎኝ ኮበለለ
ይህ በድን ስጋዬ ፍፁም ከኔ ራቀ እኔን ተነጠለ

ያየሁሽ ቀን ድባብ ትዝታ ጭሮብኝ እንዲያ ስቅበዘበዝ
ከትዝታ ጓዳ አንቺ ያለሽበትን እያንዳንዱን ስመዝ

ከፊቴ አይጠፋም ሁሌ ትዝ ይለኛል
ባስታወስኩሽ ቁጥር ወደር አልባው ሀሴት ዘልቆ ይሰማኛል

ይህ ሁሉ ድባቤ ይህ ሁሉ ትዝታ
ሳላብድ በፊት ነው ሳይሰማኝ ሽውታ

እና አለሜዋ......
ድጋሚ እንድደሰት ደስታ እንዲሰማኝ
ሀገሬውም ባንቺ እኔን እንዳያማኝ

ከጎኔ ሁኚልኝ የትም አትሂጂ
ዘላለም ለመኖር....
እኔ አብጃለሁ አንቺም ቶሎ እበጂ።

OB'
@jadmasse25
@The_prophetAB