Get Mystery Box with random crypto!

#ክተት ቀድሞ እሷን ስቀጥራት ገንዘቤን ለማውጣት መች አሰብኩኝ ሌላ እንዳለሽ ከለላ..... ከ | 🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻

#ክተት

ቀድሞ እሷን ስቀጥራት
ገንዘቤን ለማውጣት

መች አሰብኩኝ ሌላ
እንዳለሽ ከለላ.....

ከላይሽ አንስቶ አንቺን ስነካካ
የፍርሀት ድንበር ስሜቴን ሲያንኳኳ

ክተት አለኝና የጓደኛ መጥፎ
የተንኮል ሀሳብን በሀሳቤ ፅፎ

ልክተተው ይቅርብኝ እያልኩ ሳመነታ
ክተተው የሚል ድምፅ ሰማው በሽውታ።

እኔም ከተትኩላት እሪታው ቀለጠ
ውስጤ እየፈራ ቀልቤ እየተናጠ
በስተመጨረሻ
ብሩን ቆጠረና ገንዘብ ለኔ ሰጠ።

አዬ ቴክኖሎጂ......

ATM ማሽኑ እንዴት ተበላሽቷል
ገንዘብ መውለድ ትቶ ጩኸቱ በርትቷል።

የባላገር ነገር ጉዳዩን አላውቀው
ክተት ሲሉኝ ብቻ ከትቼ ከትቼ
ሜዳ ነው ምወድቀው።

OB' (ja)
@jadmasse25
@The_prophetAB