Get Mystery Box with random crypto!

-------------  ሸበላው  --------- ❴ Part-3 ❵ (የመጨረሻ ክፍል)        | 🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻

-------------  ሸበላው  ---------

Part-3 ❵
(የመጨረሻ ክፍል)

       ይኸው እስካሁን ድረስ ውጪ ባደርኩ ቁጥር እናቴ አየጮኸችብኝ 25 አመት ሞላኝ። ከሴቶች ጋር እንደ feminist ተሟጋች ስሞላፈጥ ህይወቴን መግፋት እየመረረኝ ሳለ እንዳጋጣሚ ሆኖ በስራ ምክንያት ከአንድ የሀብታም ልጅ ጋር ተገጣጠምኩ። እስቲ የእኔንም የእናቴንም ህይወት ልቀይር ፣ በዛውም ወግ ማዕረግ ላሳያት ብዬ ከልጅቷ ጋር ተጠቃለልኩ። ልጅቷ ልታብድልኝ ትንሽ ነው የቀራት። የርሷ ፍቅር ደግሞ እጅ እጅ ይላል ። ሀገር ሰላም ብዬ ተኝቼ ለሊት ላይ ተሳስቼ አይኔን ብገልጥ ቁጭ ብላ እያፈጠጠቺብኝ ነው ማገኛት። ስንት ጊዜ አስደነገጠቺኝ። ሁሌ ቁርስ ምሳ እራት አብሪያት ካልበላው ወይ ተሳስቼ ውጪ ከበላው ቤቱን መቅደላ ነው ምታደርገው። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ቢሮ ሆኜ ትን ሲለኝ እራሱ ውሀ ይዛ አጠገቤ ቆማ አገኛታለው። ከሁሉም ከሁሉም ደግሞ የከበደኝ ሁሌ ማታ ማታ ፍቅር መስራት አለብን የምትለው ነገር ነው። እንዴ .. ልገለኝ ነው ሀሳቧ? .. ፆም አትል ፣ ወርሀዊ ግዴታ አትል .. እንደ ሸማኔ እንዝርት ስውረገረግ እንዳድር ነው የምትፈልገው። የመጨረሻ ያንገሸገሸኝ ግን መፀዳጃ ቤት ብቻህን አትገባም ያለቺኝ ቀን ነበር። ለካ ፍቅርም ሲበዛ እንደዚህ ያንገሸግሻል። አልፀልይም እንጂ ብፀልይ ኖሮ "አቤቱ የዚህችን ልጅ ፍቅር በልኩ አርግልኝ" የሚል ቃል አክልበት ነበር።
   እንደመታደል ሆኖ ከዚህ ሁሉ ሴቶች በኋላ አንድ የምትጠላኝ ሴት አገኘው። እናቷ (ማለትም አማቼ) ። ባየቺኝ ቁጥር ደሟ ይፈላል። ከልጇ ጋር ስንጋባ ደስተኛ አልነበረችም እንድንፋታም የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። አጠላሏን በጣም ነበር ምወድላት (ተጠልቼ አላቅማ) ። ታዲያ በስተመጨረሻ የልጅቷም ፍቅር ሲበረታ የእኔም ትዕግስት ተሟጦ ሲያልቅ የእናቷም ነገረኛነት ሲታከልበት የፍቺያችን ቀን ደረሰና ተፋታን። የፍቺያችንን እለት ለማክበር ብዙ አንዕስቶች ተገኝተው ነበር። የሚገርመው ነገር ግን ከእነሱ ውስጥ በጣም ደስተኛ የነበረችው አማቼ ነበረች። አትታዘቡኝና የዛን እለት ከእርሷ ጋር ነበር ያደርኩት። የሚያበሽቀው ነገር ግን  ለሊት ላይ ተሳስቼ አይኔን ስገልጥ እንደ ሞኝ እያፈጠጠቺብኝ ነበር። አይ እድሌ!

አይቀጥልም

miky