Get Mystery Box with random crypto!

ቅምጥሏ ቅምጥል አፍቅሬ ለሷ ተቸግሬ ኩሽና እንዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ሳስ | Agaren yaye

ቅምጥሏ

ቅምጥል አፍቅሬ
ለሷ ተቸግሬ
ኩሽና እንዳትገባ ካልጋ እንዳትነሳ
ምግብ አብሳይ ቀጠርኩ ሳስብላት ለሷ
የእንጀራ ጠርዝ ጣቷን እንዳይቆርጣት ብዬ
አጉራሽም ቀጠርኩኝ አሳቢ መስዬ
ቅምጥሏን ፍቅሬን ድንገት ቢያስነጥሳት
ይማርሽ የምትል ሌላም ቀጠርኩላት
የሞልቃቃ ነገር አያምር መጨረሻው
ቅጥ ያጣዉን ፍቅሬን ውስጤን ስላየችው
ባል ቀጥረህ አምጣልኝ ብላኝ አረፈችው

Share ለቅምትሏ

https://t.me/Ethiopian_Dating_Channel