Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_ሆይ! “ከገዛ ራስህ ሕይወት በላይ ሚስትህን አፍቅራት፡፡ እውነተኞች ኹኑ እንጂ በፍጹም አት | መርጌታ መንግስቱ ባህላዊ መድሀኒት ቀማሚ

#ባል_ሆይ!

“ከገዛ ራስህ ሕይወት በላይ ሚስትህን አፍቅራት፡፡ እውነተኞች ኹኑ እንጂ በፍጹም አትለያዩ፡፡ በውጭ ከመቆየት ይልቅ ከሚስትህ ጋር በቤትህ አብረሃት ማሳለፍን ምርጫህ ይኹን፡፡ አክብራት፤ በግልፅም አድንቃት፡፡ ጥፋት ስታጠፋ በትዕግሥት ምከራት፡፡ አብራችሁ ጸልዩ፡፡ አብራችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዱ፡፡ አብራችሁ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ንባባትና ስለ ጸሎት ተወያዩ፡፡ ትዳራችሁ እንደዚህ ከኾነ የቅድስና ሕይወታችሁ ከመነኰሳት ሕይወት ጋር የሚነጻጸር ነው (ይኾናል)፡፡” 
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ሚስቶች_ሆይ

“ባሎች ቅናተኞችና የሚያመነዝሩ እንዲኾኑ የሚያደርጋቸው እናንት ሚስቶች ባሎቻችሁን ለንጽህና ስለማታነሣሡዋቸው ነው፡፡ እናንተ ዘማውያን ሴቶች በሚያጊያጊጡበት ሽልማት ባሎቻችሁ ደስታን እንዲፈልጉ ስለምትገፋፉአቸው ነው፡፡ በዚሁ ምክንያትም ፈጥነው በዚሁ ነውር ይጠመዳሉ፡፡ አንቺ ባልሽን ይህን እንዲንቀውና በንጽህና፣ በፈሪሐ እግዚአብሔርና በትሕትና ደስታን ማግኘት እንዲፈልግ ብታስተምሪው ኖሮ በቀላሉ እንደዚህ ወዳለ ነውር ራሱን አይከትትም ነበር፡፡ ጋለሞታ ሴት ከአንቺ በላይ ልታጌጥ ትችላለች፡፡ በምግባር በሃይማኖት ግን አይደለም፡፡ ስለዚህ ከጋለሞታ ሴት ሊያገኘው በማይችለው ጌጥ ደስታን እንዲያገኝ አስተምሪው፡፡ ... ከዚያ በኋላም ባልሽ ጸጥተኛ ይኾናል፤ ያከብርሻል፡፡ እግዚአብሔርም ይህን በማድረግሽ ምክንያት ቸርነቱን ያበዛልሻል፡፡ ሰዎችም ኹሉ ያደንቁሻል፤ በወዲያኛውም ዓለም ሰማያዊ በረከትን ትቀበያለሽ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE