Get Mystery Box with random crypto!

የሲኖዶሱ ፍጻሜ እና ድራማው በሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ዙሪያ የመጀመሪያው ውይይት በዚህ ሰአት ይሾም | ድምፀ ተዋሕዶ (VoT)

የሲኖዶሱ ፍጻሜ እና ድራማው

በሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ዙሪያ የመጀመሪያው ውይይት በዚህ ሰአት ይሾም አይሾም የሚል ነበር። በኋላም መሾም እንዳለበት ተወሰነ።
ቀጣዩ አጀንዳ በሁሉም ቦታዎች ይሾም ወይስ በኦሮሚያ በኩል ብቻ የሚለው ነበር። ብዙዎቹ ከሁሉም ቦታ እንዲሾም ሐሳብ ሰጡ። ከፖለቲከኞች አጀንዳ የተቀበሉት ደግሞ ከኦሮሚያ በኩል ካልሆነ ብለው ድርቅ አሉ። በፖለቲከኞቹ በኩል ከኦሮሚያ ብቻ ለምን ተፈለገ?
ፖለቲከኞች ሲኖዶሱ ውስጥ የአማራ ማንነት ያላቸው አባቶች ይበዛሉ ብለው ያምናሉ። በዚህም ምክንያት በሲኖዶሱ ውስጥ የፖለቲካውን አጀንዳ ለማስፈጸም ከኦሮሚያ የተገኙ ጳጳሳት መብዛት አለባቸው። አሁን ከኦሮሚያ ብቻ ከተሾመ ከነባሮቹ የአማራ ብሔር ተወላጅ ከሚባሉት ጳጳሳት ጋር ተወዳዳሪ ቁጥር ስለሚኖራቸው ውሳኔውን ለመቀልበስ አቅም ያገኛሉ።
በዚህም መሠረት ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ብቻ እንዲሾም ውሳኔ ላይ ተደረሰ። ቁጥሩን በተመለከተም ጭቅጭቅ ተነሣ። ብሔርተኛ ጳጳሳት ብዙ ቁጥር ያለው ኦሮሞ ጳጳስ እንዲሆን ተከራከሩ። በመጨረሻም 7 ከኦሮሚያ 2 ከደቡብ እንዲሆን ተወሰነ።
በዚህም መሠረት ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገው ሳይሆን ለፖለቲከኞች የሚጠቅመው ውሳኔ ተወስኗል። እስካሁን ባለው ሁኔታ ፖለቲከኞች 100% ግባቸውን መተዋል።
ሌላው አንገብጋቢው ጉዳይ ከዘጠኙ ውስጥ ሕገ ወጦቹ አሉ ወይስ የሉም የሚለው ጉዳይ ነው።
ተሿሚዎቹን በተመለከተ መልምሎ የሚያቀርብ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሟል። ይህ ኮሚቴ 7 ጳጳሳትን የያዘ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 85% የኦሮሞ ማንነት ያላቸው፣ 15% የአማራ ማንነት ያላቸው ናቸው። የኦሮሞ ማንነት ካላቸው ውስጥ ሕገ ወጡን ቡድን የሾሙት እነአባ ሳዊሮስ ይገኙበታል።
ታዲያ ይህ ኮሚቴ ቀጣይ እነማን ሊሾሙ እንደሚችሉ አያሳችምን?
በዚህም አለ በዚያ እውነታው አንድ ነው። አበው ቤተ ክርሰሰቲያኗን ለፖለቲከኞቹ አሳልፈው ሰጥተዋታል። የፖለቲከኞች አጀንዳ ታይቶ ለፖለቲከኞች በሚስማማ መልኩ ውሳኔ ተላልፏል።
በጉባኤው ዋጋ የከፈሉትን፣ መሃል ሰፋሪ የነበሩትን እና የፖለቲከኞችን አጀንዳ ለማስፈጸም ትግል ያደረጉትን በዝርዝር ይዘን እንመጣለን።

ድምፀ ተዋሕዶ
https:/t.me/onesinod