2023-05-19 15:34:16
ነገ በአዲሱ ፕላን የመስጅድ መስሪያ ይሰጠናል ይለኛል ወይ ጉድ
ይሄ ታሪክህን መለስ ብለህ አለማወቅ ነው።
በሃገራችን በአዲስአበባና ዙሪያው ትግል ያልተደረገባቸው መስጅዶች አሉ??
የሰው ህይወት ያልተከፈለባቸው መስጅዶች አሉ?
በየእለቱ ክፍለከተማም ሆነ ከተማ መስተዳድር በር ላይ ተሰልፈው ፈቃድ ይሰጠን፣ ካርታችን አላልቅ አለ፣ የቦታ ይዞታችን ባለበት ይሁንና ሌሎችም መሰል ጥያቄ ይዘው የሚጠይቁ የመስጅድ ኮሚቴዎችን አታውቅም?
ኧረ የትኛው መስጅድ ነው ካርታው በእጅህ ተሰጥቶህ የሚያውቀው?
ዛሬ የሚፈርሱ መስጅዶችህ ህገወጥ የሚል ታፔላ ተሰጥቷቸዋል። ትናንት የብዙ መስጅዶች የትግል ታፔላ ይሄው ነበር።
በገፅህ በቋንቋህ ዛሬ መቃወም ካልቻልክ እመነኝ ነገ ለምነህ አታገኘውም። አንተ መስጅድ ሰርተህ ስትሰግድ ማየት ህመሙ የሆነ የመንግስት አካል ዛሬም አለ። ትናንትም ነበር። ነገም ይኖራል።
ስለዚህ ድምፅህን አሰማ። በነገርህ ላይ የአንተ መስጅድ ሲፈርስ አካባቢው ላይ ያለ የሌላ እምነት ቤተእምነት አልተነካም።
ለምን ብለህ ጠይቅ?
ካርታ ያለው መስጅድ ፈርሷል ለምን ብለህ ጠይቅ?
ቢያንስ ፃፍ በፌስቡክ አጀንዳነት ብዙ ጉዳይ ተቀይሯል። በኮሜንትም ጠይቅ። ይህ ጉዳይ የመስጅድ ነው። የኔ ያንተ ሳይሆን የአላህ ቤት ነው። ወደጎን መመልከቱን ትተህ የአላህ ወገን ሁን!!
@ Abu khenifa
1.3K views12:34