Get Mystery Box with random crypto!

ቲክቶክ በአሜሪካ ሊታገድ ይችላል? የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሀገሪቱ ውስጥ የቲክቶክ ተንቀ | Ethiopian Digital Library

ቲክቶክ በአሜሪካ ሊታገድ ይችላል?

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሀገሪቱ ውስጥ የቲክቶክ ተንቀሳቃሽ ምስል ማጋራትና ማየትን  ወደ መከልከል ሊያመራ የሚያስችለውን ረቂቅ ላይ እፈርማለሁ ማለታቸው ተሰምቷል።

ባይደን ቲክ ቶክን በአሜሪካ ውስጥ የሚከለክለውን ረቂቅ  ኮንግረሱ ካፀደቀው ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ነገር ግን የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ 170 ሚሊዮን አሜሪካውያን የሚጠቀሙበትን አገልግሎት መከልከል ፍትሃዊ አይደለም አስጊም ነው ብለዋል።

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት በሙሉ ድምፅ ርምጃውን ካፀደቀ በኋላ በቲክቶክ ላይ በተከፈተው የማዘጋት ዘመቻ ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ  ወይም ረቡዕ  ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ቲክቶክን በአሜሪካ ለመከልከል የተዘጋጀው ረቂቅ እንዲፀድቅ የምክር ቤቱን ሁለት ሶስተኛ ድምጽ ማግኘት እንዳለበት መገለጹን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library