Get Mystery Box with random crypto!

ብሄራዊ መታወቂያ ያላገኘ ሰው የማህበራዊ አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ መ | Ethiopian Digital Library

ብሄራዊ መታወቂያ ያላገኘ ሰው የማህበራዊ አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸው ተገለጸ

የብሄራዊ መታወቂያን የያዘ ማንኛውም ማህበረሰብ የትኛዉንም አገልግሎት እና ማንነቱን ማረጋገጥ የሚፈልግበት አገልግሎት ላይ መጠቀም እንደሚችሉ ተነግሯል።

የብሄራዊ መታወቂያ ኮሚንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት  ይሄንን መታወቂያ እንደ አንድ የአገልግሎት አማራጭ አድርገው ይጠቀሙበታል ማለት  እንጂ፣ ማህበረሰቡ ብሄራዊ መታወቂያ ከሌለው ምንም አይነት አገልግሎት አያገኝም ማለት እንዳልሆነ  ተናግረዋል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከሶስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሰው የብሄራዊ መታወቂያን ለማግኘት ምዝገባ እንዳከናወነ ታውቋል።

የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አቤኔዘር፣ማህበረሰቡ ስለብሄራዊ መታወቂያ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛው ምንጭ ማግኘት እንዳለበትም አሳስበዋል።
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library