Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ከሁሉ ስፖርት የስፖርት ውርርድ ተቋም ጋር ለሁለት አመታ | Daily Sport - Ethiopia

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ከሁሉ ስፖርት የስፖርት ውርርድ ተቋም ጋር ለሁለት አመታት የሚቆይ የአጋርነት ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አድርጓል።

ይህ አጋርነት የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ለማበረታታት ታስቦ የተደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የሊጉን ተወዳጅነት እና ፍላጎት እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የገንዘብ ድጋፍ ያካተተ ሲሆን በተጨማሪም ሁሉ ስፖርት የመጫወቻ ኳስ እና የተለያዩ አልባሳትን ለህክምና ቡድን፣በሜዳ ላይ ለሚሰሩ ለሚዲያ ሰራተኞች፣የስታዲየም ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እና የሊግ ኮሚቴ አባላት ማቅረብን ያካትታል።