Get Mystery Box with random crypto!

#UPDATE አብንን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እንደታ | Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

#UPDATE

አብንን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እንደታሰሩ ቤተሰባቸው ተናገሩ
የምክር ቤት አባሉ ትናንት ምሽት ከመኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ መታሰራቸው ተገልጿል
አብንን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ እንደታሰሩ ቤተሰባቸው ተናገሩ።
በ2013 በተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸው ተናግሯል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ቤተሰብ አባል ለአልዐይን እንዳሉት ከሆነ "ትናንት ጥር 22 ቀን 2016 ዓ .ም ምሽት 3:30 ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት የጸጥታ ሀይሎች መጥተው ደሳለኝ ጫኔን ለጥያቄ እንፈልግሀለን ብለው ወስደውታል" ብለውናል።
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ የነገሩን እኝህ የቤተሰብ አባል የፌደራል ፖሊሶቹ ለጥያቄ እንፈልግሀለን ከማለት ውጪ ምንም ያሉት ነገር የለም ሲሉም ነግረውናል።
ዛሬ ጠዋት ጀምሮም ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥተው ፍተሻ በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ሰምተናል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጀይላን አብዲ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡን ላቀረብንላቸው ጥያቄ "አሁን ላይ ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም" ሲሉ ተናግረዋል።
ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡
የፌደራል መንግሥት ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለማብቃቱም ሆነ መራዘሙን አስመልክቶ ያወጣው መረጃ የለም
#አልአይን
#Follow
facebook 1 :- https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900&mibextid=2JQ9oc
facbook 2:- https://www.facebook.com/asharamedia24
Youtbe :- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw
telegram:- https://t.me/asharamedia24
Watsapp:- https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T