ጣፋጭ ድላችን በአገው ፈረሰኞች በአል ላይ በተግባር ሲታይ .. የኢትዮጵያ አርበኞች የነፃነ | Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
ጣፋጭ ድላችን በአገው ፈረሰኞች በአል ላይ በተግባር ሲታይ ..
የኢትዮጵያ አርበኞች የነፃነት ተጋድሎ ቋሚ መታሰቢያ ሐውልት በመሆን በየዓመቱ የሚከበረውን የአገው ፈረሰኞች በዓል በቦታው አክብረናል::
በዓሉን ከዘመኑ የነፃነት ተዋጊወች (የፋኖ) አመራር እና ሰራዊት እንዲሁም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ተመራቂወች ጋር ስናከብር ልዩ ኩራት ተሰምቶናል::
84ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል በተከበረበት በዚህ ዕለት የ84ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል የአምባሳደርነትን ማዕረግ ከፈረሰኞች ማህበር አባል እጅ ተረክበናል::
አምባሳደርነቱ ለመላው የአማራ ፋኖ የተሰጠ እንደመሆኑ መጠን ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል የአርበኞችን ታሪክ ደግመን ደጋግመን በመፃፍ ኃላፊነታችንን እንወጣለን!
አስረስ ማረ