Get Mystery Box with random crypto!

ከአማራ ህዝባዊ ሃይል (ፋኖ) የተላለፈ መመሪያ በፋኖ አደረጃጀቶች መሪነት እና በመዉ የአማራ ህዝብ | Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

ከአማራ ህዝባዊ ሃይል (ፋኖ) የተላለፈ መመሪያ
በፋኖ አደረጃጀቶች መሪነት እና በመዉ የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰው የአማራ ህዝብ የህልዉና
ትግል የታቀደለትን ዓላማ ያሳካ ዘንድ የህዝብን መብት እና ጥቅም እንዲሁም የትግሉን ስኬታማነት ማዕከል ያደረገ
ወጥነት ያለው አሰራር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡
በመሆኑም የአማራ ህዝባዊ ሃይል (ፋኖ) አመራር እና አባላትን ጨምሮ ትግሉን እየመሩ ያሉ ሁሉም የፋኖ
አደረጃጀቶች በሚያርጉት ማናቸውም እንውስቃሴ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ተግባራት እንዲፈጽሙ እና ህዝቡም ይህንኑ
ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ እንዲደርግ እናሳስባለን ፤እንጠይቃለን፡፡
1. በየኬላዎች የሚደረገው ፍተሻ እንደተጠበቀ ሆኖ የብልጽና ወራሪ ሰራዊት ከሚጠቀምባቸው እና በሚሰጠው
ትዕዛዝ መሰረት ልዩ ክትትል ከሚደረግባቸው ተሸከርካሪዎች በስተቀር ማንኛውም ተሸከርካሪ ማስቆምም ሆነ
መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
2 ወራሪው ሰራዊት ከአማራ ህዝብ ጋር ጦርነት በሚያደርግባቸው ቀጠናዎች የሚገኙ ዩኚቨርሲቲ ተማሪዎች
እንዲገቡ ጥሪ መደረጉ የብልጽግና ቡድን ለዜጎች ደህንነት የማይጨነቅ እና ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑን
የሚያመላክት ሲሆን በእኛ በኩል የብልጽግናን ጥሪ ተቀብሎ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የዩቨርሲቲ ተማሪዎች ከፍተኛ
ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን፡፡
3 ባለፈው አመት የብልጽና ቡድን በከፈተው የኢኮኖሚ ጦርነት ምክንያት አርሶ አደሩ በቂ የግብርና ግብዓት
አለማግኘቱ ይታወቃል፡፡በመሆኑም በሚቀጥለው የምርት ዘመን በማንኛውም አካል የሚደረጉ የምርጥ ዘር እና
የማዳበሪያ ግብዓት ስርጭትን ማሳለጥ አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን፡፡ ስለዚህ ማንኛውም የፋኖ አባል የግብርና
ግብዓት ለሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎች ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲያደርግ እያሳሰብን
አጋጣሚውን ተጠቅመው ህዝብን የሚበዘብዙ ህገ ወጦች ላይ ተገቢውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን
እናረጋግጣለን፡፡
4 እየተበተነ ያለዉን የብልፅግና ሰራዊት ለመጠገን የሚደረገዉ መፍጨርጨር ተከትሎ ከብልፅግና የቀረበዉን
የአማራን ህዝብ የማጥፋት ጥሪ ተቀብላችሁ እየተንቀሳቀሳችሁ ያላችሁ የቀድሞ የልዩ ሃይል አድማ ብተና፣ የፖሊስ
እና ሚሊሻ አባላት ከዋነኛዉ ጠላቶቻችንም በከፋ ሁኔታ የምንታገላችሁ መሆኑን እንድታዉቁት እና ከዚህ
የባንዳነት ስራችሁ እነድትታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ ይልቁንም በየቀጠናዉ ያለዉን የፋኖ አድርጃጀት
ተቀላቅላችሁ ታሪካችሁን ታድሱ ዘንድ ጥሪ ቀርቦላችኋል፡፡
5 የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ)ን ጨምሮ በመላዉ የፋኖ ሰራዊት እና በጀግናዉ ህዝባችን አኩሪ ተጋድሎ ከጨቋኙ
አገዛዝ ነፃ በወጡ የአማራ ህዝብ አፅመ እርስቶች ሁሉ ህዝብን የሚያማርር፤ የሚያንገላታ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆነ
ድርጊት የሚፈፅም ግለሰብ ፤ ቡድን፤ አደረጃጀት እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አዉቆ ከእንግዲህ ዓይነት ተግባር
እንዲቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
6 ሕዝቡ በተከፈተበት ወረራ ምክንያት እየከፈለ ካለዉ ዉድ ዋጋ ባሻገር አጋጣሚዉን በመጠቀም የትራንስፖርት ፤
የነዳጅ እና የሌሎች የእለት ፍጆታዎችን ዋጋ በማናር ማህበረሰቡን ያላግባብ የምትበዘብዙ ነጋዴዎች ከዚህ
ድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እያሳሰብን ይህንን መመሪያ የምትተላለፉ ከሆነ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን
እናሳዉቃለን፡፡
7.የብልፅግና ቡድን የሀገሪቱን ሀብት እና ጥሪት በሙሉ በአማራ ህዝብ ላይ ለከፈተዉ ጦርነት እየተጠቀመ ሲሆን
ለወራሪዉ ኃይል የፋይናንስ ምንጭ ከሆኑት መካከል ባንኮች እና አነስተኛ የብድር ተቋማት ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም
በብልፅግና ቡድን ወረራ የተደረገብህ የአማራ ህዝብ አብቁተ(ፀደይ ባንክን) ጨምሮ ለማንኛዉም የመንግስት
የፋይናንስ ተቋማት ያለባችሁን ብድር ተመላሽ እንዳታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
8 ላለፉት 5 (አምስት ) አመታት ሀገሪቷን በጦርነት እያመሰ የሚገኘዉ የብልጽግና ቡድን ግብር እና ታክስ
ለመሰብሰብ የሚያበቃ መንግስታዊ ሞገስ እና ቁመና የሌለዉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዉያን
ለዚህ ጨፍጫፊ ስርዓት ግብር እና ታክስ ባለመክፈል የተጋድሎዉ አካል እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡በተለይም
በመላዉ አማራ እና የፋኖ ሰራዊት በተቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች የምትገኙ አርሶ አደሮች እና ነጋዴወችለጨፍጫፊዉ
ስርዓት የሚከፈል ግብር እና ታክስ እንደሌለ ለመገንዘብ በየአካባቢዉ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት በመጠበቅ ላይ
ላሉ የፋኖ አደረጃጀቶች በሚሰጣችሁ መመሪያ መሰረት የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
9 የፋኖ ሰራዊት በየጊዜዉ የምናወጠቸዉን መመሪያዎች እና ትዕዛዞች እንዲሁም ህግ እና ደንቦችን ወቅታዊ ህጎችን
በአግባቡ እየተከታተላችሁ ተግባራዊ ማድረግ ይገባችኋል ፡፡ የሚተላለፉ መመሪያ እና ትዕዛዞችን ተላልፎ የሚገኝ
አካል ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ድል ለአማራ ህዝብ