Get Mystery Box with random crypto!

ከ50 መቶ በታች ያመጡ የ12 ክፍል ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ የትምህርት ሚኒስቴር በ | Lebu secondary school

ከ50 መቶ በታች ያመጡ የ12 ክፍል ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር ወስኗል።

በዚሁ መሠረት፤ በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡና እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመማር ያመለከቱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚቻል መሆኑንም ገልጿል።

Website፦ https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444