Get Mystery Box with random crypto!

Lebu secondary school

Logo saluran telegram alem0911466404 — Lebu secondary school L
Logo saluran telegram alem0911466404 — Lebu secondary school
Alamat saluran: @alem0911466404
Kategori: Pendidikan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 2.13K
Deskripsi dari saluran

Teachers & students information

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru

2023-04-27 20:51:30
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@tikvahethiopia
719 views17:51
Buka / Bagaimana
2023-03-22 21:04:23 የተወደዳችሁ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ
1.9K views18:04
Buka / Bagaimana
2023-03-05 15:10:41
2.4K views12:10
Buka / Bagaimana
2023-02-13 18:29:28
5.5K views15:29
Buka / Bagaimana
2023-02-13 18:29:28 ከ50 መቶ በታች ያመጡ የ12 ክፍል ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር ወስኗል።

በዚሁ መሠረት፤ በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡና እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመማር ያመለከቱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚቻል መሆኑንም ገልጿል።

Website፦ https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444
2.7K views15:29
Buka / Bagaimana
2023-02-06 21:56:43 29/05/2015

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et
2.9K views18:56
Buka / Bagaimana
2023-01-26 21:05:51
ቀን 18/5/2015 ዓ.ም


የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።


የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።


በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ፣ በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
3.5K views18:05
Buka / Bagaimana
2023-01-18 23:05:41 እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
3.4K viewsedited  20:05
Buka / Bagaimana
2023-01-04 21:27:05
4.1K views18:27
Buka / Bagaimana
2022-12-03 21:22:21
6.2K views18:22
Buka / Bagaimana