2023-05-21 21:13:19
በዚህ ቻናል ውስጥ ብፁዓን አባቶቻችን እንዳላችሁ እናውቃለን። የነገው ቀን ካወቃችሁበት በታሪክ ስማችሁ ጎልቶ የሚጻፍበት፣ ካላወቃችሁበት ግን በነፍስም በሥጋም የምትጠየቁበት ነው።
አባቶቻችን በደማቸው አጽንተው ያቆይዋትን ቤተ ክርስቲያን እናንተ ለብሔርተኛ አሳልፋችሁ ከሰጣችሁት ስለ ሃይማኖቱ ዋጋ የሚከፍለው ንቁ ኦርቶዶክሳዊ ከእናንተ ትከሻ ላይ አይወርድም። የትኛውም አይነት ጫና ቢደርስባችሁ ጫናው ሊያሸንፋችሁ አይገባም። ሞት እንኳን ቢመጣ ብትሞቱ ለክብራችሁ ነው። እናንተ የሞታችሁት እኮ የመነኮሳችሁ ዕለት ነው።
በስብሰባችሁ ውስጥ
1, ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚታገሉትን
2, ለፖለቲካ የቆሙትን
3, በዝምታ ውስጥ ሆነው በሁለት ቢላ የሚበሉትን ለይተን አውቀናቸዋል። ስም የማንጠቅሰው የጉባኤያችሁ ፍጻሜ እስከሚደርስ መታገሱ ተገቢ ስለሆነ ነው።
በመጨረሻም፣ ስለ እውነት ቆማችሁ የመነኮሳችሁላትን እና ዓለምን የተዋችሁላትን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቃላችሁ ወይስ ለፖለቲካ በመሸጥ ታሪካችሁን አበላሽታችሁ የምትመሩትን ምእመን ታሳዝናላችሁ!
ብፁዓን አበው መልሱን ለእናንተ ትተናል። ጥቁር ልበሱ ስትሉን ጥቁር ለብሰን ያነባነው ከፊት ስለተሰለፋችሁልን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ሟች መሆናችንን ስናረጋግጥላችሁ ነው።
ቤተ ክርስቲያን ከእናንተም ከማንም በላይ ናት። አደራችንን ተቀብላችሁ ስማችሁን በወርቅ ቀለም እንደምትጽፉ ተስፋ እናደርጋለን።
ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/onesinod
16.7K views18:13