Get Mystery Box with random crypto!

Tech talk with solomon kassaa

Logo saluran telegram httpstechchannal — Tech talk with solomon kassaa T
Logo saluran telegram httpstechchannal — Tech talk with solomon kassaa
Alamat saluran: @httpstechchannal
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 1.17K
Deskripsi dari saluran

Tech 24

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2023-04-04 18:49:26 #​​Cloud_Storage

[Cloud_Storage]ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት #Microsoft, #Google, and #Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

'ባክአፕ ክላውድ' በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው::
567 views@ëýū, 15:49
Buka / Bagaimana
2023-01-17 19:43:27 #የዌብሳይት_ጥቆማ

የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ

#5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች

(ብዙ መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት)

᎐ Stanford Engineering Everywhere(SEE)

ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ሲሆንነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።

᎐ MIT Open እና Courseware

የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው #የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች #የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።

᎐ GitHub.com

GitHub በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።

᎐ W3 Schools

ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።

በተጨማሪም #በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።

᎐ Codecademy

አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ #ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።



ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት...
1.4K views@ëýū, 16:43
Buka / Bagaimana
2023-01-16 00:22:05 የሶፍትዌር ጥቆማ - BatteryMon

ላፕቶፕ ስንገዛ መጀመርያ ከምናያችው ነገሮች አንዱ #ባትሪ ነው። ባትሪውን እየተጠቀምንበት የሚቆየውን ጊዜ ለማወቅ ብንፈልግ ደግሞ BatteryMon የሚባለውን ሶፍትዌር መጠቀም እንችላለን።

. በመጀመርያ ሶፍትዌሩን ከስር በማውረድ ኮምፒውተሩ ላይ እንጭናለን።

. በመቀጠል ሶፍትዌሩን ከፍታችሁ የባትሪ ምልክቷን ወይም Info -> Battery Information ትነኩና ከሚያመጣው መረጃ ዉስጥ Design Capacity እና Full charge capacity ታያላችሁ።

Design capacity የሚለው ባትሪው ከካምፓኒው ሲወጣ እንዲይዝ የታሰበው የቻርጅ መጠን ሲሆን Full charge capacity የሚባለው ደሞ አሁን ላይ ባትሪው የመያዝ አቅሙ ነው።

ባትሪው #አዲስ ከሆነ Design capacity እና Full charge capacity አንድ አይነት ቁጥር ነው የሚሆነው። ትንሽ ባትሪው ከቀነሰ ደሞ ከ1000 እስከ 3000 ያህል ልዩነት ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን ከዚያ በላይ ልዩነት ካለው ባትሪው አዲስ አይደለም ማለት ነው።

ይህ ማለት ግን አዲስ ላፕቶፕ የሚሸጡበት ቦታ ላይ ለሰው ሲያሳዩ በሚከፍቱበት ጊዜ በተደጋጋሚ ቻርጅ ሳይሰኩ ከተጠቀሙበት ሊቀንስ ይችላል። በዚህ ምክንያት አሮጌ ነው ማለት አንችልም።

አንድ ባትሪ ሞተ የሚባለው Full charge capacityው 0 ሲደርስ ነው።



መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #unmute ያደረጋችሁት #mute በማድረግ ተባበሩን "

መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።


︎●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●● ︎
ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ

1.1K views@ëýū, 21:22
Buka / Bagaimana
2023-01-13 19:51:41 ብዙ ጊዜ Delete አልሆን ያሉ Folderዎችን ማለትም permission የሚጠይቁትን ለምሳሌ window old ፋይሎችን ከኮምፕዩተራችን ላይ እንዴት አድርገን እንደምናጠፋ እናያለን..
━━━━━━━━━━━━━━━
: https://t.me/httpstechchannal
━━━━━━━━━━━━━━━
Stepዎችን በመከተል ማስተካከል ትችላላቹ......

Step
Folder/File ጋር Right Click አድርገን Properties የሚለውን ይምረጡ።

Step
ከዛም Security የሚለው ላይ Advanced የሚለውን ይንኩት።

Step
Administration ከሚለው አጠገብ Change የምትለዋን ይጫኑ።

Step
ከዛም Advanced የሚለውን ይመርጣሉ።

Step
ከዛም Find Now የሚለውን ተጭነው ከሚመጡት ዝርዝር ውስጥ የኮምፒውተርዎን User Name ይመርጡ።

Step
መቀየሩን ካረጋገጡ በኋላ ሳጥኖቹ ላይ ያድርጋሉ።

Step
Apply የሚለውን መምረጥ

Step
Messages box ያመጣል ከዛም yes ይበሉ።

Step
Permission ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ OK ይበሉት።

Step
OK ብለው ሁሉንም window ፕሮግራሞችን ይዝጉት።

Step
መጨረሻ ላይ file ላይ አድርገውት Shift + Del ይንኩት ሙሉውን ያጠፋዋል።

━━━━━━━━━━━━━━━
: https://t.me/httpstechchannal
━━━━━━━━━━━━━━━
1.2K views@ëýū, 16:51
Buka / Bagaimana
2022-12-08 05:51:31 Android መተግበሪያ ለማበልጸግ መሰረታዊ መያዝ ያለባቸው ነገሮች(ለጀማሪዎች)
..............................................

ቋንቋ መማር

Java እና XML ሁለቱም ለ #Android መተግበሪያ ወሳኝ ቋንቋዎች ናቸው። ስለዝህም የነዚህ ቋንቋ እውቀት የ #Android መተግበሪያ ለማበልጸግ የሚያስፈልጉህ ቅደመ ሁኔታዎች ናቸው።
በ Java ላይ መሰረታዊ ማወቅ ከሚገባህ ነገሮች ውስጥ:
Packages
Objects & classes
Inheritance & interfaces
Strings & numbers,generics,
Collections
Concurrency

በ Java እና በ XML ላይ ጥሩ ግንዛቤ ከያስክ አሪፍ መተግበሪያ በመጨረሻም ታበለጽጋለህ።

መተግበሪያውን እንድታበለጽግ ከሚረዱህ ቱሎች ጋር መግባባት

ከነዚህ ቱሎች(IDE) ጋር ነገረ ስራቸውን ማወቅ ባጣም ጠቃሚ ነገር ነው ፣ ይህም በፍጥነት መተግበሪያውን እንድታበለጽግ ይረድሃል።
ከነዚህም ቱሎች መሃል Android
Studio IDE አንዱ ነው።

የመተግበሪያውን ምስረታ ክፍፍል ላይ እውቀት መያዝ (Application Components)

የመተግበሪያው ኮምፖነንት መተግበሪያው መተግበሪያ ሆኖ እንዲወጣ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ፣ በሌላ አማርኛ እነዚህ ኮምፖነንቶች የመተግበሪያው ገንቢ አካል ናቸው።
እያንዳንዳቸው ኮሜፐነንቶች የየራሳቸው ሚና አላቸው፣ አንዳንዶቹ በሌላ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ።
እነዝህም ኮምፖነንቶች:
Activities
ባጭሩ, የመተግበሪ የስክሪን ገጽ እንደማለት ነው፣ የተወሰነ ስራ/ተግባር የሚፈጽም። ለምሳሌ የቴሌግራም መተግበሪያ ሲጫን የሚመጣው "እንኳን ደህና መጣህ" አንድ Activity ሲሆን ቁጥር አስገብተህ የምትመዘገብበት ደሞ ሌላ Activity ነው።

Services
ይህ ደሞ ከዃላ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ረጅም ሰዓት የሚወሰድ ተግባር ላይ ተመራጭ ናቸው።
ምሳሌ: ሙዚቃ እያዳመጥክ ቴሌግራም ስትጠቀም ወይም ሌላ ነገር ስትጠቀም ፣ መዚቃው ግን ከዃላ መጫወቱን ቀጥሏል፣ ይህ የ Service አንዱ ምሳሌ ነው።

Content providers
ይህ ደሞ አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ ቋት ላይ ትክረቱን ያደርጋል, ዳታውን በተለያዩ ፎርማት ይቀመጣል: በፋይል ሲስተም, ድህረገጽ ላይ, በ SQLite የመረጃ ቋጥ ላይ።

Broadcast receivers
ይህ ኮምፖነንት ደሞ በመተግበሪያህ ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሁን በስልክህ ሲስተም ጭምር ነው የሚከታተለው። ምንም የሚታይ ገጽታ የለውም።
መተግበሪያውን ዘግተ ወተህ ግን ከመተግበሪያው notification ሲደርስህ ይህ አንዱ የዚህ ተጽዕኖ ነው።
ይህ ኮምፖነንት ለሌላ ኮምፖነንት እንደ መግቢያ በር ሆኖ ያገለግላል።

Activating components

በ Threads, Loaders እና Tasks ላይ ጥሩ ግንዛቤ መያዝ
1.6K views@ëýū, 02:51
Buka / Bagaimana
2022-11-28 18:19:11 እንዴት ከ telegram spam መውጣት እንችላለን

በመጀመሪያ ወደ @spambot, በመሄድ start እንለዋለን ከዛም this was wrong please releas me now and son. ሚለውን መንካት
በመቀጠል this is mistake ከዛም no ! I never did that ሚለውን መንካት

Then telegram asks for you to submit a complaint. እንደዚህ ይለናል

ከዛም ይሄንን መፃፍ
No! I never spammed on groups at all. But sometimes I send invitation links yo my friends because I want them to join the channel or the group. And the admin of the group don't want it and reports me. So I must be released this must be a mistake. Thank You!

ከዚያም ይሄን message መላክ ከተላከ ከ 3 ወይም ከ 4 ሠአት ቡሀላ ይስተካከላል

#Share
1.5K views@ëýū, 15:19
Buka / Bagaimana
2022-11-27 16:57:21 አፕ ማውረጃው አልሠራ ላላችሁ ይሄንን link ተተቀሙ
1.4K views@ëýū, 13:57
Buka / Bagaimana
2022-11-27 16:56:16 Check out "True Messenger"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.truechat
1.3K views@ëýū, 13:56
Buka / Bagaimana
2022-11-25 18:55:19 አሰልቺ እና አላስፈላጊ የኤስኤምኤስ(sms) መልክት ላስቸገራችሁ ፍቱን መድሃኒት

እነዚህን መልክቶች ለማስቀረት ትሩ ሜሴንጀር የተሰኘ አፕሊኬሽን የሚያስፈልግ ሲሆን ከጥቅሞቹ መካከል:-Key Features of True Messenger–>You can block a name, block series of number from sending you sms ማንኛውንም ስም እና ቁጥር መልእክት እንዳይልኩ መከልከል ያስችላል–>Easily detect spam numbers በቀላሉ ተመሳሳይ የማስታወቂያ ቁጥሮችን ማወቅ ይችላል–>unveils names of numbers not stored in your phone በቀፏችን ላይ ያልመዘገብናቸውን ቁጥሮች ከነስማቸው ያሳየናልHow to Block all Spam Messages ይህን አፕሊኬሽን ተጠቅመን እንዴት ኤስኤምኤስ መልክቶችን መከልከል እንችላለን?==>Download True Messenger ትሩ ሜሴንጀር አፕሊኬሽን ከዚህ እናወርዳለን here==>Install True Messenger https://t.me/apkpure.com . አፕሊኬሽኑን ስላካችን ላይ እንጭናለን==>Launch it and it will ask for your number fill your correct number which is in your phone and click Get started. ከዛ እንከፍተው እና ስልክ ቁጥራችንን በማስገባት እንመዘገባለን ==>Click Yes to confirm your number ስልክ ቁጥራችን ትክክል መሆኑን እናረጋግጣለን==>Fill your name and your email in the next page, Click Continue. በሚቀጥለው ገፅ ላይ ስማችንን እና ኢሜል አድራሻ መሙላት==>On the Next window select all those message you regard as spam and Click Mark all as spam የሚቀጥለው ዋና ገፅ ላይ አላስፈላጊ የሆኑ የመልእክት ቁጥሮችን እንመርጣለን።ይህን ስናደረግ አፕሊኬሽኑ ከዚ በኅላ የመዘገብናቸው ቁጥሮች መልእክት ሲልኩ ስፓም የሚል ቦታ በማስቀመጥ ከረብሻ ይከለክልልናል ማለት ነው።
1.4K views@ëýū, 15:55
Buka / Bagaimana
2022-11-19 22:08:52 የዓይን ማዉዝ ነዉ በአይኖት touch ማረግ ይችላሉ
1.4K views@ëýū, 19:08
Buka / Bagaimana