2022-10-29 16:55:00
ለት/ቤታችን የትምህርት ማህበረሰብ በሙሉ ዛሬ ጥቅምት 19/2015ዓ.ም የትምህርት ቤታችን ዲስፕሊን ኮሚቴ የዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የተማሪዎች የስነ ምግባር ደንብ አፈፃፀም እና ክትትል በተመለከተ ያለበት ሁኔታ ላይ ተወያይቷል። በዚህም የስነ-ምግባር ደንብ አከባበር እና አፈፃፀም በተሻለ ሁኔታ እየሄዱ ቢሆንም፤ በአንዳንድ ተማሪዎች ዘንድ በቸልተኝነት የትምህርት ቤት ባህል እና ስነምግጋባር አፍፃፀም ላይ ክፍተቶች ታይተዋል። እነዚህም:-
1ኛ: አንዳንድ ተማሪዎች የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ሳያሟሉ መገኘት
2ኛ: አንዳንድ ተማሪዎች በት/ቤት ስልክ ይዞ መገኘት
3ኛ: የተወሰኑ ተማሪዎች የፀጉር አቆራረጥ እና አሰራር በተሰጠው መመሪያ መሰረት አለመሆን
4ኛ: የቤት ስራ እና ፕሮጀክት በቤት አጠናቆ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ከመደበኛው ክፍለግዜ በፊት ገቢ አለማድረግ
5ኛ: Pass Card በአግባቡ አለመጠቀም
6ኛ: ከሰዓት በኋላ ከ8:00 አርፍዶ መምጣት
7ኛ: የቆሻሻ ቅርጫቶችን በአግባቡ አለመጠቀም
8ኛ: አንዳንድ ተማሪዎች የዩኒፎርም ሱሪ ወደላይ ማጠፍ/ስኪኒ ማድረግ፣ ተመሳሳይ ቀለም ያላቸው ነገር ግን ዩኒፎርም ያልሆኑ ጉልበታቸው ላይ ኪስ ያላቸው/እግራቸው ላይ ላስቲክ ያላቸው ሱሪዎች መልበስ
9ኛ: ከት/ቤት ሲመጡ/ወደቤት ሲሄዱ የትራፊክ ደንብን በጠበቀ መልኩ አለመጓዝ(ግራ ይዞ አለመሄድ)
የታዩ ክፍተቶች ሲሆኑ፤ እነዚህ ክፍተቶች የታዩባችሁ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ በወጥነት እንድታስተካክሉ በጥብቅ እያሳሰብን ለትውስታ ይረዳችሁ ዘንድ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ የተሰጡ ስልጠናዎችን እና መመሪያዎችን በድጋሚ ከዚህ ማሳሰቢያ ጋር አብረን አያይዘናል።ወላጆች የት/ቤቱ ህግ እና ደንብ በአግባቡ እንዲተገበር በቤት አስፈላጊውን ክትትል እንድታደርጉ አበክረን እያሳሰብን ይህ በእንዲህ እንዳለ ስልካቸው ለትምህርት አገልግሎት ትስስር (parent link) ከተፈጠረላቸው እና ገደብ ከተደረገላቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጭ ስልክ ይዞ መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
ባጠቃላይ ሁሉም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ የተገለፁ መመሪያዎችን እና ደንቦችን የመፈፀም እና የማስፈፀም ሃላፊነታቸውን ያለመሸራረፍ እንዲወጡ በጥብቅ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
ጥቅምት 19-2015ዓ.ም
612 views13:55