Get Mystery Box with random crypto!

ሁላችሁም ልታነቡት ይገባል ፋራ ነኝ እንዴ ግን አስታውሳለሁ ወደ ዩንቨርሲቲ ማለፌን ሳረጋ | Hahu

ሁላችሁም ልታነቡት ይገባል

ፋራ ነኝ እንዴ ግን

አስታውሳለሁ ወደ ዩንቨርሲቲ ማለፌን ሳረጋግጥ አንዳንድ አዝናኝ አስተያየቶች ደርሰውኝ ነበር ግን ከማልረሳው ውስጥ አንዱን ላካፍላቹህ
አንዱ ምን አለኝ መሰላቹህ ?

" በቃ የግቢ ቺኮችን ልትፈጃቸው ነዋ ?" አለኝ
ቺክ ማለት ምን ማለት ነው? ብዬ ልጠይቅ ፈልጌ ነበር ግን ሳስበው ለካ ግቢ ልገባ ነው እናም በቃ ፋራ መባል ስላልፈለኩ ስቄ አለፍኩት ።

ለዛሬው ርዕስ መነሻ የሆነኝ ግን የሆነ ህፃን ልጅ ( ህፃን መስሎኝ ነበር) ያለኝ ቃል ነው ።
ጩጬው ምን አለኝ መሰላቹህ?
"  እስካሁን ግን ስንት ጠበስክ ? " አለኝ 
በኩርኩም አናቱን ልጠብሰው አስቤ ነበር ሳስበው ግን ከመምታቴ ይልቅ ቀስ ብዬ ባስተምረው ጥሩ ነው በሚል እሳቤ
* ቤቢዬ ዩንቨርሲቲ ውስጥ እኮ ወንድና ሴት አብሮ መሆን አይችልም ፡ ያስባርራል * ብዬ ስፎግረው
" ተዪው በቃ ሙዓ 'ፋራ ነሽ ' መሰል" አላለኝም ?
°አይ የዘንድሮ ልጅ° እያልኩ በአግራሞት ተፋታሁት
የሚገርመው እኮ ልጁ ገና የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ነው ( ውይይ ረስቼው ለካ 6ት ላይ ሁሉንም ነገር ጨርሰው ነው ወደ ሰባት የሚያልፉት)

Hooooooo

በቆሎ መሰሉት እንዴ ሴቶቹ?(ለነገሩ  በቆሎም ተወዳለች )

አስረኛ ክፍል እያለሁ የሆነ አዝግ አማርኛ አስተማሪ ነበር ያስተማረኝ፧፧ እናም አስተማሪያችን  የህይወት ታሪካችሁን ፃፉ ብሎን የምፅፈው ሳጣ የሆነ ታሪክ ፈጥሬ ቀበጣጠርኩ ።

ከፅሁፌ ላይ ያስተምሪውን ብሎም የጓደኞቼን ቀልብ የሳበው ደግሞ:-
ሁለተኛ ክፍል እያለሁ ገራሚ የፍቅር ታሪክ ነበረኝ ብዬ የቀባጠርኩት ልብወለድ ነበር
ያኔ ብዙ የልብወለድ መፅሃፍትን አነብ ስለነበር በሬ ወለድ ታሪኬን እውነተኛ ለማስመሰል ብዙም አልተቸገርኩም ነበር ።

እናም የህይወት ታሪኬን አስተማሪዬ ከሰማ በኋላ
" የምርህን ነው ግን ?" አለኝ

እኔም እምባዬ እየመጣ
እስካሁን ድረስ  በልቤ አለች ስለ ልጅቷ ሳስብ ምግብ አይበላልኝም ....

ምናምን ብዬ ስፎግረው በጣም ተገርሞ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ " እና አሁን አንተ ዩንቨርሲቲ ልትሄድ ነው? " አለኝ

^ፋራ ነው እንዴ ?^



እና እኔ ምን ላርግ ምንም አይነት የህይወት ታሪክ አልመጣ አለኛ፤ በዛ ላይ 20 ማርክ አለው ብሎ ገገመ ።

ለማንኛውም አርፎ መማር ወይም የፍቅር ጓደኛ አለመያዝ ፋራ የሚያስብል ከሆነ ፡ ሆነ ነው እንግዲህ ምን ማድረግ ይችላል?
በቃ ፋራ እየተባላችሁም ቢሆን አርፋቹህ ተማሩ
አራዳ እንደሆናቹህ ግን ውስጣችሁን ደጋግማቹህ ንገሩት

በነገራቹህ ላይ እኔ አራዳም ፋራም አይደለሁም ፤ እርድናና ፋርነት ለኔ እስካሁን ግልፅ አልሆኑልኝምና

እናንተ ግን በራሳቹህ አለም አራዳ ለመሆን ሞክሩ
በተለይ አዲስ ተማሪዎች አራዳ ነህ ወይም እሷ እኮ ጭስ ናት ምናምን እያሉ የሚበሏችሁን  ባልሰማ ላሽ በሏቸው ፤  ፋራ ተብሎ ግንባራቹህ ላይ እስካልተፃፈባቹህ ድረስ ፋራ መባል ለናንተ ተራ የሲኖትራክ ክላክስ እንደሆነ ቁጠሩት።

Muja እንደጻፈው

 @Hahuethiopia