Get Mystery Box with random crypto!

ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB]

Logo saluran telegram fkerofficial — ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB]
Logo saluran telegram fkerofficial — ኤልሳ[FB]™ _____________________Elsa[FB]
Alamat saluran: @fkerofficial
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 1.75K
Deskripsi dari saluran

የ ኤልሳ[FB] ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል እነሆ
♥♥♥
በዚህ ቻናል የ ኤልሳ[FB]ን የስነ- ፅሁፍ ስራዎች በብቸኝነት እንዲሁም ሌሎች ውብ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ
AMAZING QUOTES
MIND QUESTIONS AND OTHERS!
ግጥም
ድርሰት
አጫጭር አባባሎች ፍልስፍናዎች እና ሌሎችም!
@fkerofficial
ELSA[FB] OFFICIAL CHANNEL !

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2023-05-14 22:11:40
154 views19:11
Buka / Bagaimana
2023-05-14 19:48:48
265 views16:48
Buka / Bagaimana
2023-05-13 21:47:42 ዋጋ



በኤልሳ[FB]


ክፍል - 3

........" አዎ ፊዮሪ ነች !"
"ዋው ይገርማል ! ግን እኮ ስሟን እንጂ ታሪኳን በዝርዝር አላጫወትከኝም" አለኝ እጁን በደረት እያጣመረ
" ታሪኳ ረጅም ነው ዮኒ "
" ይሁና... ይነገረኝ ! መቼም እዚህ እንዳድር የፈለከው በምክንያት ነው "
" እሱማ አዎ..."
" እኮ ንገረኛ.."  አቀማመጡን ለመስማት እያመቻቸ እጅ በደረቱን አውርዶ ከጎኑ ያለውን ትራስ አቅፎ በጉጉት አይን አይኔን ያየኝ ጀመር
ሁሌ ሳስታውሰው ወደሚፀፅተኝ ታሪክ በትዝታ ፈረስ የኋሊት ገሰገስኩ....

" ከአመታት በፊት ነው የ ሀይስኩል ተማሪ ነበርኩ ያኔ አባቴን አላውቀውም ነበር የምኖረው ከአንድ ደሀ እናቴ ጋር ነበር... ፊዮሪን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት 10ኛ ክፍል የመጀመሪያ ቀን ክላሳችን የገባን ቀን ነበር...  ሳያት እንዴት እንደደነገጥኩ... ያ ስሜት እና ድንጋጤ እስካሁን ለሴት ልጅ ተሰምቶኝ አያውቅም የመጀመሪያዬም ስለነበር ይመስለኛል.... ከዛ በቃ ምን ብዬ እንደምግባባት ማሰብ ጀመርኩ... ግን ግራ ገባኝ አብራት ክፍላችን የገባችው ጓደኛዋ የትምርትቤቱ ተፅእኖ ፈጣሪ ናት....  ሀብታም ከመሆኗም በላይ ቆንጆና የትምርትቤቱ ዳሪክተር ወንድም  ልጅ ነበረች  ይሄን ሁሉም ያውቃል ከኔ ጋር ደግሞ ከሰላምታ ያለፈ ምንም የለንም...  ቢሆንም ፊዮሪን ለመግባባት ብቸኛዋ አማራጭ መሰለችኝ...
ግን ከሰላምታ ያለፈ ንግግር ፈጥሬ እንዴት እንደምግባባት ስጨነቅ አንድ ቀን ራሷ አየችኝና ሰላም አለችኝ..  ከፊዮሪ ጋር ነበሩ ሰላም አልኳትና አጋጣሚውን ተጠቅሜ ፊዮሪንም አቅፌ ሰላም አልኳት... እንዴት እንደደነገጠች ብታይ?..
ነገሩ እኔም አስቤበት አልነበረም... ብቻ ፊዮሪም ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች በጥናትም በምንም ሰበብ አብረን ከማሳለፍ አልፈን የማንለያይ 3 ጓደኛሞች እስከመሆን ደረስን ግን ይህ ሁሉ ሲሆን የሚሰማኝን ማንም እና ማንም አያውቅም ነበር... "
"እሺ ከዛስ?" አለኝ ፈገግ እያለ
" ልንገራት አልንገራት እያልኩ በማመነታበት ወቅት አንድ ቀን ከሌሎች ቀናት በተለየ በጠዋት እኩል ክፍል ደረስን አጋጣሚውን ተጠቅሜ......"


ይ.
ቀ..
ጥ..
ላ....
ል......
.
.
@fkerofficial
448 viewsedited  18:47
Buka / Bagaimana
2023-05-13 21:46:42
427 views18:46
Buka / Bagaimana
2023-05-11 20:58:48 ዋጋ


በኤልሳ[FB]

ክፍል - 2


.........ራሷ ናት... ፊዮሪ ራሷ...
"ችግር አለ? " አለችኝ መነፅሯን እያወለቀች
"አ..አይ ..." ብዬ እጇን ለቀኳትና "ይቅርታ አንዴ መጣሁ " ብዬ ወደሆቴሉ መታጠቢያ ክፍል ገብቼ ፊቴን ታጠብኩ ... ፊትለፊቴ ያለውን መስታወት አየሁት ምን እየተሰማኝ እንደሆን እንኳን አላውቅም... ፍርሀት ድንጋጤ ፍቅር ፀፀት አላውቅም... እሷስ አውቃኝ ይሆን? ወይ የት ነው የማውቀው እያለች ይሆን? ረስታኝ ይሆን? ብዙ ጥያቄዎችን በራሴ ላይ አወራረድኩበት... ግን ሳስበው ለዛ የሚሆን ጊዜ የለኝም ራሴን " ተረጋጋ ቆፍጠን በል " አልኩት
ተመልሼ ወደ መቀመጫዬ ሄጄ ተቀመጥኩ አምሮባታል የሚለው ቃል አይገልፃትም ተቀይራለች ፍፁም አዲስ ሰው ሆናለች...
" ጥሩ እንግዲህ እሷ አለቃዬ ፊዮሪና ጌታቸው ናት አብሯችሁ የሚሰራው ድርጅት ባለቤት እና ዋና ስራ አስኪያጅ ስትሆን እኔ ደግሞ ማኔጀር ነኝ......." እያለች ስለስራ ጉዳይ ማውራቷን ቀጠለች እንኳን የምትለውን ልሰማት ለምን እንደተገናኘን እንኳን ማሰብ አቃተኝ ቀና ስል  ዮኒ በጣም ግራ በተጋባ አስተያየት ሲያየኝ አየሁት ባይኔ እንዲጠጋኝ ጠቅሼው ወደ ጆሮው ጠጋ ብዬ "ስትጨርስ ቤት ና ! " ብዬው ከመቀመጫዬ ተነሳሁ
" ወዴት ነው አቶ ናኦድ " አለችኝ ፊዮሪ ቀና ብላ ባልደረባዋም ንግግሯን ገታ አድርጋ  ተመለከተችኝ
"ይቅርታ ትንሽ ልክ ስላልሆንኩ ነው ሁሉንም ከሱጋር ጨርሱ  ዮኒ የሚፈረምባቸውን ወረቀቶች ታመጣልኛለህ !" አልኩት 
እሱም በ እሺታ ምልክት አንገቱን ነቀነቀልኝ  ፊዮሪን ለማየት ስሞክር አይኖቻችን ተጋጩ ወዲያው የመኪናዬን ቁልፍ አንስቼ ወጣሁ......

አመሻሽ ላይ የውጪ በሬ መንኳኳት ጀመረ ለምን እንደሆነ አላውቅም ልቤ ተሸበረ ከሷጋር ስለሚመጣ  ነው መሰለኝ እንደ አዲስ ሰው ናፈኩት የሚለውን መስማት አጓጓኝ ከተኛሁበት ሶፋ ላይ ተፈናጥሬ ተነስቼ የሳሎኑን መጋረጃ ገልጬ ሳይ ዮኒ ነበር የሆነ የደስታ ስሜት ተሰማኝ... ሳይታወቀኝ ፈገግ አልኩ..
መኪናውን ውጪ እንዳቆማት ሲገባ ሮጬ በሩን ከፍቼ ወጥቼ " መኪናህን አስገባት" አልኩት  መኪናውን አስገብቶ የሚገባው እንዲያድር ስፈልግ እንደሆነ ያውቃል...
ተመልሶ ወጣና ዘበኛው በሩን ከፍቶለት መኪናውን አስገብቶ ገባ ግራ እንደተጋባብኝ እይታው ያሳብቃል ፍጥጥ አለብኝ...
" ምን ሆነህ ነው? " አለኝ አይኑን ሳይነቅል
"አወራሀት? " አልኩት በጉጉት
"ማንን? "
" ኧኸ ፊዮሪን ነዋ "
"እ... ቢዝነሱን ማለትህ ነው? አዎ"
"ምን አለችህ?"
" ቆይ ቆይ ታውቃታለህ እንዴ ?"
" አንተ አላወካትም? "
"የት ላውቃት እችላለሁ?" አለኝ እግሩን ጠረጴዛ ላይ እየሰቀለ
"ሁልጊዜ የምትለኝስ?"
"ምን አልኩህ?"
" አስሬ ማን ፊዮሪ እያለ ያለቃቅስልህ የምትለኝ ነዋ"
" እንዴ እና?" እግሩን ከዘረጋበት በፍጥነት ሰብስቦ አይን አይኔን እያየኝ
"አንተ እኮ አትታመንም እሷ ናት ልትለኝ ይሆናል " በግርምት
"አዎ ፊዮሪ ነች! "

                           





.
.

@fkerofficial
609 views17:58
Buka / Bagaimana
2023-05-11 20:58:31
519 views17:58
Buka / Bagaimana
2023-05-09 21:40:14 ዋጋ


በኤልሳ[FB]


ክፍል -1




ቢሮ ተቀምጬ ምሳ የት እንደምበላ ግራ ገብቶኝ እያሰብኩ ዮናታን በሩን በርግዶት ገባ
" አንተ!... እስካሁን እዚህ ተቀምጠሀል? " አለኝ የእንግዳ  ማረፊያ መቀመጫው ላይ ራሱን እየወረወረ መልስ ሳልሰጠው ኮቴን ከተደረበበት ደርቤ ስልኬን ኪሴ ከተትኩ
" ትዝናናለህ እንዴ? የቀጠሮ ሰአታችን እኮ ደርሷል! "
" እንደርሳለን " አልኩት ጥቁር መነፅሬን እያጠለኩ"
"የቢዝነስ ሴቶች ናቸው አባቴ ቀልድ አያውቁም ለስራ ነው የሚመጡት"
" እና እኔ ለጨዋታ ነው የምሄደው?" አልኩት በትንሹ ፈገግ እንዲል ብዬ ነበር!
" አንተ ነህ ከሴት ጋር የምትጫወተው?.. አታስቀኝ እስኪ" አለኝ እልህ ያዘኝ
" ምን ያንሰኛል! "
" ማን ፊዮሪና  እያለ ሊቆዝምልህ ነው?   በል በል እዚሁ ሆነን ሊመሽ ነው ሆ..." እያለ ይዞኝ ከቢሮ ወጣ ዮኒ በጣም የምወደው የአመታት ጓደኛዬ ነው በስራ ተወጥሬ .....በፍቅር ስጨነቅ.... በትዝታ ስቆዝም ሁሌም ከጎኔ ነው ከጎኔ የማጣው በደስታዬ ቀናት ነው.. ለችግሬ እንጂ ለፌሽታዬ ትኩረት አይሰጥም ግን እወደዋለሁ ለኔ የሞቱ ቤተሰቦቼም የጓደኞቼም የእህት ወንድሞቼም ምትክ ነው አብረን ነው የምንኖረው ! .......
የኔን መኪና መስሪያቤት ትተናት በሱ መኪና ወደቀጠሮው ቦታ ሄድን ለትልቅ የቢዝነስ ጉዳይ ነው የምንገናኘው ከአዲስ ድርጅት ጋር አጋር ሆነን ለመስራት... ባለቤቷ ሴት መሆኗን ስልክ ተደዋውለን ቀጠሮ ስንይዝ ነበር ያወኩት... ለምን እንደሆነ አላውቅም የዛሬው ቀን ከሌሎቹ ቀናት በተለየ ዱካካም ነው... ለዮኒ እንኳን ከጠዋት ጀምሮ ጥሩ ሚባል መልስ ስመልስለት አልዋልኩም ለራሴ ሳስበው ገረመኝ ምን ሆኜ ነው? እያልኩ ምንም ሳናወራ ቀጠሮው ቦታ ደረስን...
ከተቀጣጠርንበት ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል ደርሰን የቀጠረችንን ሴት ፍለጋ በሩ ጋር ቆመን ስንደውል ኮርነር አካባቢ አንድ ቀይ ቆንጆ ወጣት እጇን አውለበለበችልን እና ወደሷ ሄደን ተቀመጥን
"ሰላም... ኤደን እባላለሁ አለቃዬ እየደረሰች ነው እስከዛ የሆነ ነገር እንዘዝ ብላ እጇን ለ አስተናጋጇ ከፍ አድርጋ አሳየቻት 
አዘን ምግብ እስኪመጣ ስልኬን አውጥቼ ለድርጅቴ የተላኩ ኢሜይሎች እያየሁ ድንገት...
"ይቅርታ ቆየሁ? " የሚል ድምፅ ሰማሁ ልቤ ስንጥቅ ሲል ይታወቀኛል የማውቀው ድምፅ መሰለኝ  ቀና ለማለት ፈራሁ ትንፋሼ ሲያንቀኝ ተሰማኝ ድንገት ለሰላምታ የተዘረጋ ቀጭን እጅ ፊት ለፊቴ ታየኝ....  ቀና ብዬ ሰላም አልኳት ጥቁር መነፅር አድርጋለች...
ስሟን ለመስማት እንደ ትውውቅ....
" ናኦድ " አልኳት
" ፊዮሪና " አለችኝ እጇን መልቀቅ ተሳነኝ የማየውን ማመን አቃተኝ ጭራሽ በሌላኛው እጇ መነፅሯን ስታወልቅ በድንጋጤ መብረቅ እንደመታው ሰው ደርቄ ቀረሁ ! ራሷ ናት... ፊዮሪ ራሷ....
ይ....
ቀ........
ጥ.........
ላ..............
ል.................



    

                                                   በኤልሳ[FB]
@fkerofficial
722 viewsedited  18:40
Buka / Bagaimana
2023-05-09 21:40:03
620 views18:40
Buka / Bagaimana
2023-05-08 18:39:48
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው " ዋጋ " ነገ ምሽት በ @fkerofficial ይጀምራል !
1.0K viewsedited  15:39
Buka / Bagaimana
2023-05-06 20:57:58
የኔ ጣዖት

አልክድም
አፍቅሬህ ነበረ ልቤ እስኪሰወር
ካንተ ሌላ ፍጥረት ያለ እስከማይመስል
ምስልህን አቁሜ ስንቴ ተሳለምኩት
ድምፅህን ቀርጬ ስንቴ ደጋገምኩት
ጣዖቴ አድርጌህ ስንቴ ነው የኖርኩት?
ባለፍክበት  ማለፍ ማእረጌ አልነበር?
ገነት እስከሚመስለኝ ካንተ መተባበር
ተሳስቶ እንኳ አይንህ የሚያያቸው
ምን ብለው ተሳሉ እንዴት ሰምሮላቸው
እኔም ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ
አካላቴን ሁሉ ለፍቅርህ ገብሬ
ከስርህ ሳልጠፋ ሆኜ እንደጥላህ
ስከተልህ...ስለምንህ... ስማፀንህ
ዳናህን ስከተል
ስርህ ስጥመለመል
አመታት አልፈዋል
ባንተ ፍቅር ምክንያት ሰውነቴን ካጣሁ
ማፍቀር በሚል ሰበብ ኖሬ ከተቀጣሁ
አሁን ግን ወሰንኩኝ በቃ አትከተለኝ
ተው ስሜን አትጥራ ውዴም አትበለኝ
ይቅርታ አትበል ምክንያት አትደርድር
እሺ ብዬ ብዞር ላታፈቅረኝ ነገር
ያፅናኝ እንጂ ልሂድ
ልንጎድ
ደሞ ሌላ ልልመድ
ካስቻለኝ ልጨክን በቃ ልሂድበት
ምንስ ባይወዳደር ሁሉም ከጣዖት

ኤልሳ[FB]

@Fkerofficial
915 viewsedited  17:57
Buka / Bagaimana