2023-05-06 23:20:22
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 በሃዋሳ የሚያደረገው ቆይታ ዛሬ በይፋ ከፍቷል።
በባህርዳር የተጀመረው የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድሬደዋ እና በአዳማ ከተሞች እስከ 22ኛ ሳምንት ቆይታውን አድርጓል። ዛሬ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ የ22ኛ ሳምንት የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ የከተማዋን የአመቱ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ተስተናግዷል። በዚህም የሃዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በ9 ሰዓት ሃዋሳ ከተማን ከሲዳማ ቡና ሲያገናኝ በ12 ሰዓት ወልቂጤ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ አገናኝቷል። በውጤቱም ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከተማን አንድ ለ ዜሮ በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን ሁለት ለአንድ ረቷል።
ከመጀመሪያው ጨዋታ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አመራሮች፣ የሲዳማ ክልል የስፖርቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የሃዋሳ ከተማ አመራሮች በተገኙበት የመክፈቻ መርሃ ግብር ተከናውኗል። በዚህም የክብር እንግዶቹ ተጫዋቾችን ወርደው በመጨበጥ ጨዋታውን ያስጀመሩ ሲሆን በቅርቡ ባንዲራውን ለሰቀለው የቀድሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ክንዴ ሙሴ በሙያ አጋሮቹ የሽኝት ፕሮግራም ተደርጎለታል።
አጠቃላይ የሊግ ውድድሩ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ቆይታውን ሲያደርግ በዛሬው እለት የታየው የሞቀ የደጋፊ ድባብ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል።
Website www.ethiopianpremierleague.net
Telegram t.me/ethiopianlea
Instagram instagram.com/ethiopianpremierleagues.c/
Twitter twitter.com/EthiopianLeague
Facebook facebook.com/ethiopianpremierleaguesc
198 viewsedited 20:20