2023-02-01 19:11:32
#የፊት ቆዳ ችግርን መለየት
የሁሉም ሰው ፊት አንድ አይነት ችግር አይኖረውም ::ስለዚህ እንደ ችግሩ አይነት መፍትሄውም ይለያያል
ሀ,ለሰፋፊ የፊት ቆዳ ቀዳዳዎች
*የቲማቲም ጭማቂ መቀባት ትንሽ አቆይቶ ሲደርቅ መታጠብ
ለ,ለፊት መጨማደድ
*ማታ የለውዝ ዘይት ፊት እና አንገት ላይ ተቀብቶ ማሳደር እና ጠዋት አብሽ ቀብቶ መታጠብ
*የእንቁላል ነጩን ክፍል መቀባት ሲደርቅ መታጠብ
*ጠዋት በባዶ ሆድ አንድ ማንኪያ ኮምጣጤ በአንድ ኩባያ ውሀ ትንሽ ስኳር ጨምሮ መጠጣት
ሐ,ለፊት ወዝ ለሚበዛ
*ሙዝ ቆዳ የሚያስፈለገው ቫይታሚን የያዘ ስለሆነ የበሰለ ሙዝ ከ2ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋ መምታት ከአይን ራቅ አርጎ ፊትን መቀባት ከ25 ደቂቃ በኋላ መታጠብ
መ,ለፊት ቆዳ ድርቀት
*2 የሻይ ማንኪያ ሽንብራ ዱቄት 4 የሻይ ማንኪያ ወተት ወተቱ የላም ቢሆን ይመረጣል ከአይን ዙሪያ ራቅ አርጎ መቀባት እና ከ 20 ደቂቃ በኋላ መታጠብ
*የእንቁላል አስኳል አንድ የሻይ ማንኪያ የለውዝ ዘይት አንድ የሻይ ማንኪያ የወተት ስልባቦት አደባልቆ መቀባት እና 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
*የበሰለ ሙዝ ማር የወተት ስልባቦት በአንድ ላይ መምታት ማታ ተቀብቶ ጠዋት መታጠብ
*የአጃ ዱቄት ከማር ወይም ከወተት ጋ መቀባት ከ 15ደቂቃ በኋላ መታጠብ
*እርጎ ለቆዳ በቂ እርጥበት ስለያዘ ንፁህ እርጎ መቀባት
ሠ,ለማድያት እና ለፀሀይ ቃጠሎ
*አደይ አበባ ቢገኝ እርጥቡን መጨፍለቅ ወይም መፍጨት ከለጋ ቅቤ ጋ መቀባት
*የአብሽ ዱቄት በለጋ ቅቤ ለውሶ ማታ ተቀብቶ አድሮ ጠዋት መታጠብ
*ጥቂት የኦቾሎኒ ፍሬዎች መፍጨት በአንድ የሻይ ማንኪያ እርጎ አደባልቆ መቀባት እና በተጎዳው ቆዳ ላይ በስሱ መለጠፍ ከ15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ
*የሩዝ ውሀ መቀባት የሚበቃንን ያህል ሩዝ አጥቦ በውሀ ለ 24ሰዐት መዘፍዘፍ ውሀውን አጥለን መቀባት ትንሽ አቆይቶ በንፁህ ውሀ መታጠብ
*እርድ በማር መቀባት
@Ethio_Hakim
@Ethio_Hakim
374 viewsedited 16:11