Get Mystery Box with random crypto!

🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻

Logo saluran telegram the_prophetab — 🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻
Logo saluran telegram the_prophetab — 🌻 የተሰበሩ አክናፍ🌻
Alamat saluran: @the_prophetab
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 265
Deskripsi dari saluran

መፅሀፍ የተዘጋ በር ሲሆን ማንበብ ደግሞ የእዛ የተዘጋው በር ቁልፍ ነው እና በር ላይ ቆማችሁ ምን ትሰራላቹ ግቡ እንጂ ……
መፅሀፍ እማያነብ ሰው ስለ መኖሩ መጠራጠር አለበት!
የተሰበሩ አክናፍ ላይ
>>> ግጥሞች
>>>>ወጎች ይቀርባሉ
ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ግጥም መላኪያ
@AbZMariyam21
>>>>>> @The_prophetAB <<<<<<<<<

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru

2023-05-05 23:10:49 ግጥም አፍቃሪ ኖት?

ፍቅር ሲጣል ደግሞም ሲነሳ
ፍቅር ሲነጥፍ ደግሞም ሲወዛ
ፍቅር ሲረገም ደግሞም ሲባረክ
ፍቅር ሲሰበር ደግሞም ሲጠገን
ፍቅር ሲኮስስ ደግሞም ሲጀግን
ፍቅር ሲከንፍ ደግሞም ሲያዘግም
ፍቅር ሲፈግግ ደግሞም ከል ሲለብስ
ፍቅር ውል ሲያስር ደግሞም ሲፈታ
የሁነቱ አካል መሆን ይሻሉ?

ብዕር እና ወረቀት አፍ ለ አፍ ገጥመው በግጥም ሲዶልቱ መታዘብ ይፈልጋሉ?
እነሆ ግዜ መግዛቱን ትተው @yeneeyita @yeneeyita @yeneeyita ን አሁኑኑ ይቀላቀሉ!

ኑ በግጥም ግጥም እንበል!
እነሆ ዕይታዬን እዩልኝ!
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
Share አድርጉ!
23 views20:10
Buka / Bagaimana
2023-04-14 18:18:42 የሕማማት ንሰሃ 3

ገጣሚ አላዛር ብዙዬ

@The_prophetAB
100 views15:18
Buka / Bagaimana
2023-02-26 22:02:56
ናዝሬት/አዳማ የመግቢያ ቲኬት ማግኘት ምትፈልጉ በ (inbox) አውሩኝ

@AbZMariyam21
167 viewsedited  19:02
Buka / Bagaimana
2023-01-12 20:32:31
@The_prophetAB
259 views17:32
Buka / Bagaimana
2022-12-23 20:11:43 ነገህን ለመኖር
ትላንትን አትርሳ
@The_prophetAB
297 views17:11
Buka / Bagaimana
2022-12-20 21:23:10 #በትር

ሙት አፅሜን ይዤ
የሙስዬን በትር በቀኝ ተመርኩዤ

ልብሽን ለመክፈል ጀግኜ ብነሳም
ላንቺ ፍቅር እንጂ በትር አላነሳም።

OB' @jadmasse25
@The_prophetAB
313 views18:23
Buka / Bagaimana
2022-11-16 21:18:10 #ያየሁሽ_ቀን_ድባብ

በተንቦለቦለው የከርቤ መአዛ
ይታወቀኝ ጀመር አንቺ ስትመጪ አካሌ ሲወዛ

የሻከረው ፊቴ የደረቀው ቆዳ
የለበስኩት ኩታ የልብሴ ቀዳዳ

አንቺ ስትመጪ በአስማት ተሰፋ
ባንቺ መምጣት ብቻ እንባ ሀዘኔ ጠፋ

ያየሁሽ ቀን ድባብ ያገኘሁሽ ለታ
ከኔ ተለይቶ ወዳንቺ ሲያከንፈው የልቤን ትርታ

ተመለስ ብለውም ከዳኝ እንደ ባንዳ ጥሎኝ ኮበለለ
ይህ በድን ስጋዬ ፍፁም ከኔ ራቀ እኔን ተነጠለ

ያየሁሽ ቀን ድባብ ትዝታ ጭሮብኝ እንዲያ ስቅበዘበዝ
ከትዝታ ጓዳ አንቺ ያለሽበትን እያንዳንዱን ስመዝ

ከፊቴ አይጠፋም ሁሌ ትዝ ይለኛል
ባስታወስኩሽ ቁጥር ወደር አልባው ሀሴት ዘልቆ ይሰማኛል

ይህ ሁሉ ድባቤ ይህ ሁሉ ትዝታ
ሳላብድ በፊት ነው ሳይሰማኝ ሽውታ

እና አለሜዋ......
ድጋሚ እንድደሰት ደስታ እንዲሰማኝ
ሀገሬውም ባንቺ እኔን እንዳያማኝ

ከጎኔ ሁኚልኝ የትም አትሂጂ
ዘላለም ለመኖር....
እኔ አብጃለሁ አንቺም ቶሎ እበጂ።

OB'
@jadmasse25
@The_prophetAB
390 viewsedited  18:18
Buka / Bagaimana
2022-10-08 20:31:46 ቅራቅንቦ ወሬ ስዘባርቅባት ይኸው አቀፈችኝ
ዝም ስል ነካችኝ
ቀጠልኩኝ ሳመችኝ::

ሁኔታ ስፍራዬን
ኮተት ልፍለፋዬን
ዝምታ እንባዬን
ልቧ ካልመዘነው
ይህ ነገር ምንድነው?

(ፍቅር)

ይህ ነገር መወደድ ነው? እንደህፃን ንፁህ
እንደፃድቅ ብፅዑ::

ታውቂያለሽ
ሁለቱንም ሆኜ እኩል ሰዓት ያውም
እንኳን ይቺ ቆንጆ
እኔ ራሴ ባየው እኔን አልወደውም::

ፍቅር

ዝም ስል ሳመችኝ
ሳወራም ሳመችኝ
ልብና ከንፈሯ እንዴት ታዘዘላት
በድምፄ ማትሰማው የኔ ቋንቋ አላት?

@The_prophetAB

               
382 views17:31
Buka / Bagaimana
2022-10-06 20:19:14 #ክተት

ቀድሞ እሷን ስቀጥራት
ገንዘቤን ለማውጣት

መች አሰብኩኝ ሌላ
እንዳለሽ ከለላ.....

ከላይሽ አንስቶ አንቺን ስነካካ
የፍርሀት ድንበር ስሜቴን ሲያንኳኳ

ክተት አለኝና የጓደኛ መጥፎ
የተንኮል ሀሳብን በሀሳቤ ፅፎ

ልክተተው ይቅርብኝ እያልኩ ሳመነታ
ክተተው የሚል ድምፅ ሰማው በሽውታ።

እኔም ከተትኩላት እሪታው ቀለጠ
ውስጤ እየፈራ ቀልቤ እየተናጠ
በስተመጨረሻ
ብሩን ቆጠረና ገንዘብ ለኔ ሰጠ።

አዬ ቴክኖሎጂ......

ATM ማሽኑ እንዴት ተበላሽቷል
ገንዘብ መውለድ ትቶ ጩኸቱ በርትቷል።

የባላገር ነገር ጉዳዩን አላውቀው
ክተት ሲሉኝ ብቻ ከትቼ ከትቼ
ሜዳ ነው ምወድቀው።

OB' (ja)
@jadmasse25
@The_prophetAB
336 views17:19
Buka / Bagaimana
2022-10-05 20:38:01 የወደደ ፍቅሩን
ሸረሪትም ድሩን
እንደማያስነካ
እንዲዚያ ነኝ በቃ::

ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካዜው
እንዲሳካ ብሎ
እውነቱን ሸጦ ነው  አፍቃሪ ለጊዜው።

“እሺ” ቢል ቢዋረድ ቢናቅም ቢዘበት
"ምንም አያመጣም" ብለሽ አትሳቂበት::

ለወናፍ ዐፍ ሁሉ ቢሆን መዘበቻው
የመጣበት ቀን ግን
በፍቅሩ ልክ ነው የአፍቃሪ ጥላቻው።

@The_prophetAB

               
317 views17:38
Buka / Bagaimana