Get Mystery Box with random crypto!

ምስባክ ወማኅሌት

Logo saluran telegram misbak_wemahlet — ምስባክ ወማኅሌት
Logo saluran telegram misbak_wemahlet — ምስባክ ወማኅሌት
Alamat saluran: @misbak_wemahlet
Kategori: Agama
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 3.62K
Deskripsi dari saluran

🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ 
👉ሰዓታት
👉ሥርዓተ ዋይዜማ ወማኅሌት
👉መዝሙር ዘሰንበት
👉ምስባክ ዘዘወትር ወዘሰንበት
👉ዝማሬያት
 👉ስንክሳር ዘቅዱሳን
👉መንፈሳዊ ትምህርት
🎯ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ።
መወያያ 👉 @Misbakgroup
ለአስተያየት 👉 @Zethewahdobot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 2

2023-07-03 06:13:02
452 views03:13
Buka / Bagaimana
2023-07-03 06:13:02
436 views03:13
Buka / Bagaimana
2023-07-03 06:13:02 ††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::

አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው::
ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል::
ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ40 ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል (አገልግሎታል):: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል::

በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ
¤ሕዝቡን አሻግሮ
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት አሕጉራተ ምስካይ (የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው:-
"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

††† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::

††† ሰኔ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
2.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (ቅዳሴ ቤቱ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

@Misbak_WeMahlet
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
494 views03:13
Buka / Bagaimana
2023-07-02 12:02:01 ምስባክ ዘቅዳሴ አመ ፳ወ፮ ለሰኔ
@Misbak_WeMahlet
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
594 views09:02
Buka / Bagaimana
2023-07-02 12:02:01
ግጻዌ አመ ፳ወ፮ ለሰኔ
@Misbak_WeMahlet
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
557 views09:02
Buka / Bagaimana
2023-07-02 12:01:24 ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ሐነጻ ወልድ ለዛቲ ቤት፤ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ።
@Misbak_WeMahlet
ወረብ
ተቀደሲ ወንሥኢ ኃይል ኦ ደብረ ምሕረት/፪/
እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ንጉሥኪ ዘያበርህ በኃይሉ ፋሲለደስ/፪/
@Misbak_WeMahlet
እስመ ለዓለም
በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት፤ጾም ተውህበት ለንሥሐ፤እስመ ለሊሁ መድኃኒነ ጾመ፤በጾም ሙሴኒ ጾመ በደብረ ሲና፤ወተናገሮ እግዚአብሔር በዓምደ ደመና በጾም፤በጾም ወኢያሱኒ በጾም ድኅነ፤በገባዖን ፀሐየ ዓቀመ፤በጾም ዕዝራኒ ጾመ በገዳም፤ወርእያ በገዳም ለቤተ ክርስቲያን፤በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት፤ርእዩ ዕበያ ለጾም።
@Misbak_WeMahlet
አመላለስ ዘእስመ ለዓለም
በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኃጢአት/፪/
ርዕዩ ዕበያ ለጾም/፪/
@Misbak_WeMahlet
ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ወኢያሱኒ በጾም ድኅነ በገባዖን ፀሐየ አቀመ/፪/
ዕዝራኒ ጾመ በገዳም ወርእያ ለቤተ ክርስቲያን/፪/
@Misbak_WeMahlet
=> እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)
  @Misbak_WeMahlet
join and share
Via ማህሌታውያን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE


@Misbak_WeMahlet
@Misbak_WeMahlet
@Misbak_WeMahlet


@Misbak_WeMahlet
    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪    
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ
496 views09:01
Buka / Bagaimana