Get Mystery Box with random crypto!

ጥበበኛዋ ሴት //// ሁል ጊዜ በህይወት መንገድ ላይ ብልኋች በአንድ ድንጋይ አንድ ወፍ ሳ | HUR Online Baltina🇪🇹

ጥበበኛዋ ሴት
////

ሁል ጊዜ በህይወት መንገድ ላይ ብልኋች በአንድ ድንጋይ አንድ ወፍ ሳይሆን በአንድ ድንጋይ ሶስትና አራት ወፍ በመምታት ይታወቃል።

ንጉሱ በአገልጋዩ ሰራ እና ትጋትና በታማኝነቷ እጅግ ተደሰተና ሊሸልማት ፈለገ። በቤተመንግስቱ ውስጥ ያለውን ውድ የተባለ ወርቅና እንቁ ሁሉ ከየተቀመጠበት ግምጃቤት አምጥተው ፊት ለፊት እንዲረድሩት አዘዘ...
ከዛም ንጉሱ አገልጋዬን አላት"ባንቺ እጅጉን ደስተኛ ነኝ..እዚህ ቤት ካለው ውድ ነገር ውስጥ መርጠሽ የነካሽው አንድ ነገር ያንቺ ይሆናል ።ለታማኝነትሽ ስጦታ ነው" አላት።
እሷም ብልህ ሴት ነበረችና ወርቅና የሚያብረቀርቁትን ዕንቁዋችን ችላ ብላ ወደ ንጉሱ ቀረበችና እጅን ያዘችው
ንጉሱም"እኔን ለምን ያዝሺኝ?" ሲል ጠየቃት
እሷም"ንጉሱ ሆይ ከዚህ ቤት ውክጥ የነካሁት አንድ ውድ ነገርየነ የእኔ እንደሚሆን ቃል ገብተሀል።ስለዚህ የቤቱን ዙሪያ ገባ ስቃኝ እጅግ ውድ ነገር አንተ ሆነህ ነው ያገኘሁት...ሁሉም ጌጣጌጥ አንተ ባለህበት ክፍል ዋጋቢስ እና ውበትአልባ ነው የሚሆነው" አለችው።
ንጉሱም በገረዷ ንግግር እና ብልህ መሆን በጣም ተደመመ እናም ቃሉን ጠብቆ አገባት።
ንጉሱን ካገባች ደግሞ ንግስት ሆነች ማለት አይደል.... ያ ማለት ደግሞ ቅድም ከቀረብላት ጌጣጌጦች መካከል አንድን ብቻ ሳይሆን ሁሉም በአጠቃላይ የራሷ ሆኑ ማለት አይደል።
ዘሪሁን ገመቹ
t.me/hur_baltina